በበረከት ጸጋዬ
35ተኛው የአፍሪካ ዋንጫ (ከታህሳስ 21 እስከ ጥር 10/2018) በሞሮኮ የሚካሄድ ሲሆን የወቅቱ ሻምፒዮን አይቮሪኮስት :ደቡብ አፍሪካ እና መሰል ሀገራት ከሚቀጥለው አመት የፊፋ የአለም ዋንጫ ቀደም ብለው በአህጉራዊ ውድድሩ ላይ የሚያሳዩት ብቃት ትኩረትን ይስባል።
በAFCON 2025 ላይ ላሉ ሁሉም ቡድኖች የዝነኛው የሚድያ አውታር ESPN የየቡድኖቹ መመሪያ እነሆ።
ምድብ A፡ ሞሮኮ፡ ማሊ፡ ዛምቢያ፡ ኮሞሮስ
ሞሮኮ
እ.ኤ.አ. በ2022 የፊፋ የዓለም ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚዎች በመሆን የአፍሪካን ሪከርድ አሻሽለዋል። 2023 ኮትዲቯር የአፍሪካ ዋንጫ በጥሎ ማለፍ ዙር በደቡብ አፍሪካ የደረሰባቸው ሽንፈት ያልተጠበቀ ነበረ። ዋሊድ ሬጉራጊ አሁንም የአትላስ አንበሶቹ መሪ ናቸው።
ቁልፍ ተጫዋች(ዎች)፡ አሽራፍ ሃኪሚ በፓሪስ ሴንት ጀርሜይን የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍልሚያ ከባየር ሙኒክ ጋር ባደረገው ጨዋታ ላይ ጉዳት ቢያጋጥመውም ለሃገሩ ጥሪ ደርሶታል። የቀኝ መስመር ተከላካዩ እንደተለመደው ዋናው ሰው ይሆናል ነገር ግን ለመክፈቻ ጨዋታዎች ብቁ ካልሆነ የቡድኑ ትልቁ ስም የሪያል ማድሪድ የክንፍ ተጫዋች/አጥቂ አማካይ ብራሂም ዲያዝ ይሆናል።
ትንበያ: ሻምፒዮን ይሆናሉ
ማሊ
በAFCON 2023 በጣም ተገማች ካልሆኑ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው ማሊ በሩብ ፍፃሜው ተጨማሪ ሰአት በአስተናጋጇ እና በመጨረሻው ሻምፒዮና ኮትዲቯር መሸነፏ አልታደለም። በመሃል ሜዳ ተሰጥኦው የተትረፈረፈ ወይም የተባረከ ነው ሚባልለት ‘ሌስ አይግልስ’ ወደ ጥሎ ማለፉ መሸጋገሩ አይቀሬ መሆኑ ከግምት ሲገባ ወደፊት እየገፉ ከሄዱ በሌሎች ላይ ብስጭትን ሊፈጥር ይችላል።
ቁልፍ ተጫዋች(ዎች)፡ እንደ ሞሮኮ ሁሉ ማሊም ከጉዳት በማገገም ሂደት ላይ ያለን ኮከብ ተጫዋቻቸው ይዘው ወደ ውድድሩ ጉዞ ያደርጋሉ። የቶተንሃሙ ኢቭስ ቢሱማ ልንመለከተው የሚገባ ሰው ነው። በቅርብ ጊዜ ከጉዳት፣ ከግል ጉዳዮች እና ከደቂቃ እጦት ጋር በመታገል ጥሩውን ቅርፅ መልሶ መያዝ ይችላል? አፍሪካ ዋንጫው መልስ ይሰጠናል። ምንም እንኳን ቢሱማ – ቢቸግረውም እና እንደሚጠበቀው የብቃቱ ጫፍ ላይ ባይገኝ ሌሎቹ
አማካዮች መሀመድ ካማራ (አል ሳድ) እና አማዱ ሃይዳራ (አርቢ ላይፕዚግ) እንዲሁም የቤሽክታሽ አጥቂ ኤል ቢላል ቱሬን መከታተል ተገቢ ነው።
ትንበያ፡ ሩብ-ፍጻሜ
ዛምቢያ
ቺፖሎፖሎ ለፊፋ የዓለም ዋንጫ ማለፍ ባለመቻላቸው
ከቀድሞው የቼልሲ አለቃ አቭራም ግራንት ጋር ከተለያዩ በኋላ በቀድሞው የመሀል ተከላካይ ሞሴስ ሲቾን ወደ ውድድሩ ያመራሉ። እ.ኤ.አ. በ2012 በጋቦን የተካሄደውን ውድድር በማሸነፍ ከAFCON ያልተጠበቁ አሸናፊዎች አንዱ መሆን ችለዋል። ምናልባትም በዚህ አጋጣሚ ወደ ጥሎ ማለፍ መሸጋገር ያስደስታቸው ይሆናል።
ቁልፍ ተጫዋች፡ ፓትሰን ዳካ (ሌስተር ሲቲ)
ትንበያ: ከምድብ ይወድቃሉ
ኮሞሮስ
ኮሞሮስ በወረቀት ላይ በኮከብ የታጀበ ቡድን ላይኖራው ይችላል፣ነገር ግን ቱኒዚያን ቀድማ በማጣርያ ምድብ አንደኛ
ሆና ወጥታለች:: ጋምቢያ እና ማዳጋስካርን መብለጥ ችለዋል:: በውድድሩ ሊናቁ አይገባም።
ቁልፍ ተጫዋች፡ ዘይዱ ዩሱፍ (አል-ፋቲህ)
ትንበያ: ከምድብ ይወድቃሉ
ምድብ ለ፡ ግብፅ፡ ደቡብ አፍሪካ፡ አንጎላ፡ ዚምባብዌ
ግብፅ
ፈርኦኖቹ በAFCON ታሪክ ውስጥ በሰባት ዋንጫዎች በጣም ስኬታማ ቡድን ናቸው። የመጨረሻው ስኬታቸው እ.ኤ.አ. በ2010 ነበር ነገር ግን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሁለት ጊዜ የፍፃሜ ተፋላሚ የነበሩ ሲሆን ሞ ሳላህ አህጉራዊ ክብርን
በማሳካት ተጠራጣሪዎቹን ዝም ማሰኘት ይፈልጋል።
ቁልፍ ተጫዋች፡ መሀመድ ሳላህ (ሊቨርፑል)
ትንበያ፡ ግማሽ ፍፃሜ
ደቡብ አፍሪካ
ባፋና ባፋና በሁጎ ብሩስ ስር ጠንካራ፣ የተቀናጀ፣ ስነስርዓት ያለው ቡድን ከገነባ በኋላ ለዚህ ውድድር ተገማች ወይም ተጠባቂ ናቸው። በጠንካራ የሀገር ውስጥ ሊግ – ቤቴዌይ ፕሪሚየርሺፕ – ደቡብ አፍሪካ በማሜሎዲ ሰንዳውንስ እና በኦርላንዶ ፓይሬትስ የቅርብ ጊዜ ስኬት ወደ አህጉራዊ ውድድር የሚያመሩ ወጣት ተጫዋቾችን በብዛት በስኳዳቸው ውሰጥ አካቷል። በወረቀት ላይ በጣም ጎበዝ ቡድን ባይኖራቸውም ለ2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ካለፉ በኋላ ግን እንደ ቡድን ኬሚስትሪ፣ ጥልቀት እና የገዘፈ በራስ መተማመን አላቸው።
ቁልፍ ተጫዋች፡ ላይል ፎስተር (በርንሌይ)
ትንበያ፡– የፍፃሜ ተፋላሚ ይሆናሉ
አንጎላ
በአፍሪካ እግር ኳስ ተኝቶ የነበረው ‘ፓላንካስ ኔግራስ’ በ2023 የሩብ ፍፃሜ ተፋላሚ ከሆነ በኋላ በቀላሉ የሚታይ አይሆንም። ሊጋቸው እንደ ደቡብ አፍሪካ ጠንካራ ባይሆንም በውጪ ካሉ ኮከቦች ተጨማሪ ተጫዋቾችን በመጥራት ጠንካራ ተፋላሚ መሆን ያልማሉ።
ቁልፍ ተጫዋች፡ ዴቪድ ካርሞ (ሪያል ኦቪዶ ከኖቲንግሃም ፎረስት በውሰት)
ትንበያ፡ ጥሎ ማለፍን ይቀላቀላሉ።
ዝምባቡዌ
ከሜዳ ውጪ ባሉ አስተዳደራዊ ጉዳዮች ከአብዛኞቹ ተፎካካሪዎቿ በበለጠ ሁኔታ የተደናቀፈችው
ዚምባብዌ በአንፃራዊነት ጠንካራ ቡድን አላት ። በፊፋ የአለም ዋንጫ የማጣርያ ዘመቻዋ ስኬት አልባ የነበረ ቢሆንም በቅርቡ ግን አቅማቸውን ያሳያል ያስባለውን ፍልሚያ ከደቡብ አፍሪካ ጋር አቻ መውጣት ችለዋል። ማይክል ኒ በቅርቡ በዋና አሰልጣኝነት በማሪያን ማሪኒካ ተተክቷል።
የዎልቭሱ ማርሻል ሙኔሲ ከጉዳቱ በበቂ ሁኔታ እንዳገገመ ቢታመንም ከቡድኑ ተለይቶ ቀርቷል። ሆኖም በቡድኑ ውስጥ አሁንም ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች አሉ።
ቁልፍ ተጫዋች፡ ታዋንዳ ቺሬዋ (ወልቨርሃምፕተን ዋንደርደርስ)
ትንበያ: ከምድብ አያልፉም
ምድብ ሐ፡ ናይጄሪያ፡ ቱኒዚያ፡ ኡጋንዳ፡ ታንዛኒያ
ናይጄሪያ
ሱፐር ኢግልስ ከሜዳ ውጪ ባሉ ጉዳዮች ዝግጅታቸው ተስተጓጉሏል፡ : በተጫዋቾች እና በናይጄሪያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መካከል በተነሳው ያልተከፈለ ጉርሻ ምክንያት በህዳር ወር እልባት ያገኘው በምን አይነት ሁኔታ እንደሆነ ግልፅ አይደለም። ኤሪክ ቼል በጥር ወር ሀላፊነቱን ከተረከበ በኋላ በሜዳው ላይ ያለውን እንቅስቃሴ አረጋግቷል ምንም እንኳን ከጨዋታው ውጪ አንዳንድ ችግሮችን መፍታት አቅቶት ነበር። ሁሉም ነገር በቁጥጥር ስር ከሆነ በችሎታ ናይጄሪያን የሚተካከሉ ጥቂት ቡድኖች ብቻ ይሆናሉ።
ቁልፍ ተጫዋች፡ ቪክቶር ኦሲምሄን (ጋላታሳራይ)
ትንበያ፡ ሩብ-ፍጻሜ
ቱንዚያ
የካርቴጅ ንስሮች እ.ኤ.አ. የ2004 ድላቸውን መድገም እንደሚችሉ ከመገመት ትንሽ ርቆ ወደዚህ ውድድር
ይገባሉ። ነገር ግን ልዩ በሆነ ፉክክር በሊግ ፕሮፌሽናል 1 የተጠናከረ እና በአውሮፓ ውስጥ ባሉ በርካታ ተጫዋቾች የታገዘ ጠንካራ ቡድን ሆነው ቀጥለዋል።
ቁልፍ ተጫዋች ሀኒባል መጅሪ (በርንሌይ)
ትንበያ፡ ጥሎ ማለፍ ዙርን ይቀላቀላሉ።
ኡጋንዳ
ክሬኖቹ ከ2019 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ AFCON ማለፍ የቻሉ ሲሆን ከባፋና ባፋና ጋር የ
ሚወዳደር የኮከብ ጥራት ባይኖራቸውም በማጣሪያው ከምድብ አሸናፊ ደቡብ አፍሪካ በአንድ ነጥብ ብቻ አንሰው አጠናቀዋል። ልምድ ባለው ፖል ፑት እየተመራች ዩጋንዳ ከስድስት አመት በፊት ከጥሎ ማለፍ ዙር ከተሰናበተችበት
አጋጣሚ ጋር ለመመሳሰል ወይም የተሻለ ጉዞን ታልማለች።
ቁልፍ ተጫዋች፡ ባባ አልሃሳን (FCSB)
ትንበያ: ከምድብ ይወድቃሉ።
ታንዛኒያ
አጥቂው ምብዋና ሳማታ የቀድሞ ብቃቱ ላይ ስላልሆነ እና በTaifa Stars ቡድን ወረቀት ላይ እርግጠኛ ባልሆኑበት ወቅት የዘንድሮው AFCON ለእነሱ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ሆኖም፣ አሁንም ለሌሎች ቡድኖች ትልቅ ፈተና ውስጥ ማስገባት እና ወደ ጥሎ ማለፍ ዙሮች ሾልከው መግባት የሚችሉ ተጫዋቾች አሏቸው።
ቁልፍ ተጫዋች፡ Novatus Miroshi (ጎዝቴፔ)
ትንበያ: ከምድብ አያልፉም።
ምድብ መ፡ ሴኔጋል፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ ቤኒን፣ ቦትስዋና
ሴኔጋል
የቴራንጋ አንበሶች ወርቃማ ዘመናቸውን ከፍታ ለመድገም የሚያስችል ቡድን እያሰባሰቡ ነው። እንደ ሳዲዮ ማኔ እና ካሊዱ ኩሊባሊ ያሉ ተጨዋቾች አሁንም በስብስቡ ውስጥ ይገኛሉ። ነገር ግን እንደ ኒኮላስ ጃክሰን እና ኢስማኢላ ሳር የብቃታቸው ጫፍ ላይ በመገኘት ቡድኑን የመምራትን ሃላፊነትን ለመረከብ ተዘጋጅተዋል። የAFCON
2021 አሸናፊዎች (በ2022 ዘግይቶ በተካሄደው ውድድር) ወደዚህ ውድድር የሚያመሩት ቁልፍ በሆነ
የሽግግር ጊዜ ላይ ቢሆንም፣ ግን በእርግጠኝነት እንደ ቡድን የሚናቁ አይሆንም።
ቁልፍ ተጫዋች፡ ሳዲዮ ማኔ (አል-ናስር)
ትንበያ፡ ግማሽ ፍፃሜ
ዲሞክራቲክ ኮንጎ
በAFCON 2023 አራተኛ ደረጃን ከጨረሰ በኋላ ዲ.ሪ. ኮንጎ ምናልበትም ለዋንጫው ሁለተኛ ተጠባቂ ሊሆን ይችላል። ከሌስ ሌኦፓርድስ ውጭ አገር ላይ ለተመሰረቱ ባለተሰጥኦዎች ሊፎካከሩ የሚችሉ ጥቂት የአፍሪካ ቡድኖች አሉ እና ጎበዝ አሰልጣኞች በአገር ውስጥ በደረጃቸው መውጣታቸውን ቀጥለዋል። እንደ ደቡብ አፍሪካ እና ሞሮኮ የቅርብ ዓመታት ወጥነት ባናይባቸውም ፣ በቅርበት ሊታዩ ይገባል።
ቁልፍ ተጫዋች፡ አሮን ዋን-ቢሳካ (ዌስትሃም ዩናይትድ)
ትንበያ፡ ሩብ-ፍጻሜ
ቤኒን
ልምድ ባለው አሰልጣኝ ጌርኖት ሮህር እየተመራ፣ ሌስ ጉፔፓርድስ በቀናቸው ማንኛውንም ትልቅ ቡድን
ማሸነፍ ይችላሉ። ቤኒን የኮከብ ሃይል ባይኖራትም ለፊፋ የአለም ዋንጫ ለማለፍ በጥርጣር ውስጥ
ገብታለች። በመጨረሻው ቀን በናይጄሪያ ከመሸነፏ በፊት ደቡብ አፍሪካን ወደ አለም ዋንጫው እና ሱፐር ኤግልስን ወደ ጥሎ ማለፍ ውድድር ልኳል። (በጥሎ ማለፉ ማጣሪያ ናይጄሪያ በዲ.ሪ ኮንጎ ተሸንፋ ከአለም ዋንጫው ድግስ ቀርታለች።)
ቁልፍ ተጫዋች፡ አንድሪያስ ሁውንቶንጂ (ሴንት ፓውሊ በውሰት ከበርንሌይ)
ትንበያ፡ ጥሎ ማለፍ ዙር
ቦትስዋና
በአስቸጋሪ ምድብ ውስጥ ያሉት ቦትስዋናውያን በአፍሪካ ዋንጫው እምብዛም ተጠባቂ አይሆኑም። ተአምራዊ ነገር ወይም ድንገቴ ፈንጠዝያ (surprise) ሊረዳቸው እንደሚችል ተስፋ ያደርጋሉ – በማጣሪያው ላይ እንዳደረጉት፣ ማውሪታንያ እና ለዓለም ዋንጫ ያለፈችውን ኬፕ ቨርዴን አበሳጭተው ግብፅን ተከትለው በሁለተኝነት የውድድሩን ትኬት ቆርጠዋል።
ቁልፍ ተጫዋች፡ ታያዮኔ ዲትልሆክዌ (አል-ኢትሃድ፣ ትሪፖሊ)
ትንበያ: ከምድብ ይወድቃሉ
ምድብ ሠ ፡ አልጄሪያ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ሱዳን
አልጄሪያ
‘Fennecs’ AFCON 2019 አሸንፈዋል እና በእርግጠኝነት በድጋሚ ፈታኞች ናቸው። የክለባቸው እግር ኳስ በጠንካራ አቋም ላይ ይገኛል። ነገርግን ከፍተኛ ችሎታቸው በቭላድሚር ፔትኮቪች የቡድኑ ጥራት ምክንያት አውሮፓን መሰረት ያደረገ ነው። በጠንካራ የኋላ አደረጃጀቷ እና ለመሰባበር አስቸጋሪ በመሆኗ የምትታወቀው አልጄሪያ በውድድሩ ሩቅ ልትጓዝ ትችላለች። የአፍሪካ ሃያላኖች ከሩብ ፍፃሜው አንስቶ ሲፋለሙ የሚፈጠረው ነገር ለመተንበይ አስቸጋሪ ቢሆንም አልጄሪያ ይህን ያህል ርቀት ካላጠናቀቀች ግን ትልቅ ድንጋጤ ነው።
ቁልፍ ተጫዋች ሪያድ ማህሬዝ (አል-አህሊ)
ትንበያ፡ ሩብ-ፍጻሜ
ቡርኪናፋሶ
ቡርኪናፋሶ በቅርብ ጊዜ በተደረጉ የአፍሪካ ዋንጫዎች በከፍታና በዝቅታ ሪከርድ አስመዝግባለች። እ.ኤ.አ. በ 2013 ሁለተኛ ደረጃን ካጠናቀቁ በኋላ በ2015 ከምድብ ማለፍ አልቻሉም ነበረ። በ2017 ሶስተኛ ሆነው አጠናቀቁ፤ በ2019 ማጣሪያውን ማለፍ እንኳ አልቻሉም። ያለፉት ሁለት ውድድሮች በካሜሩን አራተኛ ሆነው
ሲያጠናቅቁ እና ከ2 አመት በፊት በጥሎ ማለፉ ዙር በሻምፒዮኖቹ ኮትዲቯር ተሸንፈዋል። አሁን በብቃታቸው ጫፍ ላይ አይደሉም፣ ነገር
ግን ሳይጠበቁ ሃያላኑን ሊገነድሱ ይችላሉ።
ቁልፍ ተጫዋች፡ በርትራንድ ትራኦሬ (ሰንደርላንድ)
ትንበያ፡ የጥሎ ማለፍ ዙር
ኢኳቶሪያል ጊኒ
ኢኳቶሪያል ጊኒ በመጨረሻዎቹ ሁለት ውድድሮች ሩብ ፍፃሜውን እና የጥሎ ማለፍ ዙሩን መቀላቀል ችለው ነበረ። በዚህ ጊዜ በተፎካካሪ ቡድን ውስጥ ይገኛሉ – ግን ሾልከው ለመውጣት ይቸገሩ ይሆናል። የእነሱ ምርጥ ማሳያ እ.ኤ.አ. በ 2015 በሃገራቸው አፈር አራተኛ ሆነው ማጠናቀቅ መቻላቸው ነበር።
ቁልፍ ተጫዋች: ሳውል ኮኮ
ትንበያ፡ ጥሎማለፍ ዙር
ሱዳን
ምንም እንኳን ኩሩ የእግር ኳስ ታሪክ ያላት ሀገር ብትሆንም ሱዳን ግን እንደ አንዳንዶቹ ተጠባቂዎች ሆና ወደዚህ ውድድር ትገባለች። ሀገሪቱ ከኤፕሪል 2023 ጀምሮ በመካሄድ ላይ ባለው የእርስ በርስ ጦርነት ስትታመስ ቆይታለች እና በዚህ
ውድድር ላይ ድንጋጤ ከፈጠሩ ይህ ትልቅ የኩራት ምንጭ ሊሆን ይችላል።
ቁልፍ ተጫዋች፡ መሀመድ አብደልራህማን (አል ሂላል፣ ኦምዱርማን)
ትንበያ: ከምድብ ይወድቃሉ
ምድብ ስድስት፡ አይቮሪ ኮስት፣ ካሜሩን፣ ጋቦን፣ ሞዛምቢክ
አይቮሪኮስት
ዝሆኖቹ በ2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ላይ ቦታቸውን ከያዙ በኋላ እንዳለፈው ውድድር ሻምፒዮን ወደ ሞሮኮ ያቀናሉ። ኮትዲቯር በመጨረሻው AFCON ከመጀመሪያው እስከ ፍፃሜው ቆንጆ ቆይታ አልነበራትም፣ ነገር ግን መጨረሻ ላይ ውጤታማ ነበሩ እና በችሎታ የተሞላው ቡድን ለማቆም አስቸጋሪ ይሆናል። ኤመርሴ ፋዬ ቡድኑን ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ክብር የመምራት ኃላፊነት የተሰጠው ጊዜያዊ አሰልጣኝ ነበር። አሁን
በትውልዶች መካከል በሚደረገው ሽግግር ውስጥ ያለውን ጎን ይመራል ፣ ግን አሁንም በወረቀት ላይ
በውድድሩ ውስጥ ካሉት ምርጥ መካከል ይገኛሉ።
ቁልፍ ተጫዋች፡ አማድ ዲያሎ (ማንቸስተር ዩናይትድ)
ትንበያ፡ ሩብ-ፍጻሜ
ካሜሩን
የካሜሩንያን እግር ኳስ ባለፉት አመታት ውጣ ውረዶች አጋጥሞታል። AFCON 2017 ከሜዳ ውጪ ባሉ ጉዳዮች ቢታመሱም በሁጎ ብሩስ እየተመሩ የዋንጫ ባለቤት መሆን ችለዋል። በአሁኑ ወቅት የሃገሪቱ ፌዴሬሽን በዋና አሰልጣኝነት ቦታው እና በሳሙኤል ኤቶ በፌዴሬሽኑ አመራር ላይ ባደረገው ውዝግብ እንደገና ውዥንብር ውስጥ ገብቷል። የማይበገሩ አንበሶችም ከአለም ዋንጫው ጠፍተው ብልህ ናቸው ቢሏቸውም፤ ነገር ግን ሲቆስሉ ተናካሽ ወይም አንዳንዴ በጣም አደገኛ ናቸው።
ቁልፍ ተጫዋች ብራያን ምቤሞ (ማንቸስተር ዩናይትድ)
ትንበያ፡ ጥሎማለፍ ዙር
ጋቦን
ጋቦን ያለፈውን አፍሪካ ዋንጫ ማለፍ ሳትችል ከቀረች በኋላ ዳግም ወደ AFCON ተመልሳለች። በዓለም ዋንጫ ማጣሪያው ላይ ወድቀዋል፣ ነገር ግን በጣም ጠንካራ የሆኑትን ብሄራዊ ቡድኖች እንኳን ሊፈትኑ የሚችሉ የቡድን ስብስብን ይዘዋል።
ማሪዮ ሌሚና፣ ፒየር-ኤምሪክ ኦባሚያንግ እና ዴኒስ ቦዋንጋ ተጠቃሸ ናቸው። ዕድሜያቸው ሠላሳዎቹ – ይህ ማለት ቃሉን ለመፈጸም የተወሰነ ጊዜ ላለው ትውልድ ይህ ትልቅ ውድድር ነው ማለት ነው።
ቁልፍ ተጫዋች፡ ማሪዮ ሌሚና (ጋላታሳራይ)
ትንበያ፡ ጥሎ ማለፍ ዙር
ሞዛምቢክ
ምንም እንኳን ለዚህ ውድድር ተጠባቂ ባይሆኑም ማምባስ በትልልቅ ቡድኖች ላይ ድሎችን የሚያነሳሱ
ተጫዋቾችን አሏቸው ፣ በጄኒ ካታሞ በጣም ታዋቂው ስም ነው። ካሜሩንን እና ጋቦን በብቃታቸው ጫፍ ላይ
ባለመሆናቸው ወደ ጥሎ ማለፍ ውድድር መግባትን ተስፋ ያደርጋሉ።
ቁልፍ ተጫዋች፡ Geny Catamo (Sporting CP)
ትንበያ: ከምድብ ይወድቃሉ




