
(ስፖርት ኮሚሽን)

በቶኪዮ 2020 ፖራሊምፒክ ጨዋታ በ1500 ሜትር T-13 አይነስውራን ጭላንጭል ለሀገራችን የወርቅ ሜዳሊያ ያስመዘገበችው አትሌት ትዕግስት ገዛኸኝ የ2.8 ሚሊዮን ብር እና 40 ግራም የወርቅ ኒሻን ሽልማት ተበርክቶለታል ።
አትሌት ትዕግሥት ገዛኸኝ 04:23:24 በሆነ ሰዓት በመግባት ለሀገራችን የወርቅ ሜዳሊያ በማስመዝገብ በፖራሊምፒክ ጨዋታ ታሪክ መስራቷ ይታወሳል ።
የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ንጋቱ ኃ/ማሪያም 400 ሺህ ብር ሲሸለም ፤
በ1500 ሜትር እጅ ጉዳት T-46 5ኛ ደረጃን በመያዝ ዲፕሎማ ያስመዘገበው አትሌት ገመቹ አመኑ የ200ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል።
በተመሳሳይ በ1500 ሜትር አይነስውራን ጭላንጭል T-13 7ኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀው አትሌት ታምሩ ከፍያለው 150 ሺህ ብር ተሸልሟል ።
የቡድኑ ሀኪም 100 ሺህ ብር ተሸልሟል ።
በቶኪዮ 2020 ፖራሊምፒክ ጨዋታ ኢትዮጵያ በ 3 አትሌቶች የተወከለች ሲሆን 1 ወርቅ ሁለት ዲፕሎማ በማግኘት ከዓለም 59ኛ ከአፍሪካ 6ኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቃለች ።