ሁለቱ የኢትዮጵያ ክለቦች በአፍሪካ መድረክ ተጋጣሚዎቻቸውን አውቀዋል

የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ የሆኑት ኢትዮጵያ መድን በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ የዛንዚባሩን ክለብ ምላንዴግ ይገጥማሉ:: የመጀመሪያ ጨዋታቸውንም በሜዳቸው ያደርጋሉ።

ኢትዮጵያ መድን አሸናፊ ከሆኑ በሁለተኛው ዙር ከፒራሚድስ እና “APR” አሸናፊ ጋር ይጫወታሉ። 

የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ከ መስከረም 9-11/2018 እንዲሁም የመልስ ጨዋታው ከ መስከረም 16-18/2018 ሊደረግ እንደታቀደ ይታወቃል።

ወላይታ ድቻ በበኩላቸው ከአንድ የሊቢያ ክለብ ጋር እንደሚጫወቱ ታውቋል የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታም በሜዳቸው ያደርጋሉ::

ሊቢያን የሚወክለው ቡድን ያልታወቀ ሲሆን በቀጣይ ሀገሪቷ ይፋ እንደምታደርግ ይጠበቃል።

የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ከ መስከረም 9-11/2018 እንዲሁም የመልስ ጨዋታው ከ መስከረም 16-18/2018  የሚካሄድ ሲሆን ወላይታ ድቻ በደርሶ መልስ የሚያሸንፉ ከሆነ ከግብጹ አል መስሪ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

  • Brook Genene

    Brook is a football writer who focuses on sports injuries. He has previously written on local sports for Soccer Ethiopia and Ethiopian Business Review magazine.

    Related Posts

    የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ዳሰሳ

    በበረከት ጸጋዬ 35ተኛው የአፍሪካ ዋንጫ (ከታህሳስ 21 እስከ ጥር 10/2018) በሞሮኮ የሚካሄድ ሲሆን የወቅቱ ሻምፒዮን አይቮሪኮስት :ደቡብ አፍሪካ እና መሰል ሀገራት ከሚቀጥለው አመት የፊፋ የአለም ዋንጫ ቀደም ብለው በአህጉራዊ ውድድሩ…

    ሞ ሳላህ ላይ እየተሰጡ ያሉ ትችቶች እንዴት ይታያሉ? 

    ግብጻዊው የሊቨርፑል የፊት መስመር ተጫዋች ሞ ሳላህ ከሊዲሱ ጨዋታ መልስ በሰጠው አስተያየት መነጋገሪያ ሆኖ ከርሟል፡፡  “ 90 ደቂቃ ሙሉ ተጠባባቂ ወንበር ላይ መሆኔን ላምን አልችልም፡፡ ለሶስተኛ ተከታታይ ጨዋታ ነው ይህ…

    You Missed

    የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ዳሰሳ

    የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ዳሰሳ

    ሞ ሳላህ ላይ እየተሰጡ ያሉ ትችቶች እንዴት ይታያሉ? 

    ሞ ሳላህ ላይ እየተሰጡ ያሉ ትችቶች እንዴት ይታያሉ? 

    ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች

    ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች

    Qatar to build 11 running tracks in 11 countries

    Qatar to build 11 running tracks in 11 countries

    በአፍሪካ ትምህርት ቤቶች የእግር ኳስ ሻምፕዮና የሴካፋ ማጣሪያ ኢትዮጵያ በሁለቱም ጾታ ለፍጻሜ አለፈች

    በአፍሪካ ትምህርት ቤቶች የእግር ኳስ ሻምፕዮና የሴካፋ ማጣሪያ ኢትዮጵያ በሁለቱም ጾታ ለፍጻሜ አለፈች

    ቀይ ቀበሮዎቹ ካታር ለመገኘት በሞሮኮ ይፋለማሉ

    ቀይ ቀበሮዎቹ ካታር ለመገኘት በሞሮኮ ይፋለማሉ