ኒኮ ዋልተማደ- በወሳኝ ሰአት የተገኘ አጥቂ

የጀርመን ብሄራዊ ቡድን የ2014ቱን የአለም ዋንጫ ካሸነፉ ማግስት አንድ ከባድ ነገርን መጋፈጥ ነበረባቸው:: ኑሮ ያለድንቁ አጥቂ ሚሮስላቭ ክሎዘ! በአሁኑ ሰአት በጀርመን ሁለተኛ ዲቪዚዮን የቡንደስሊጋ ዋንጫን ብዙ ጊዜ በማሸነፍ ሁለተኛ ላይ ያሉትን ኑረንበርግ የሚያሰለጥነው ክሎዘ በርካታ ግቦችን በአለም ዋንጫ የማስቆጠር ሬከርድን ከሮናልዶ ፊኖሜኖ ከወሰደ ማግስት የብሄራዊ ቡድን አገልግሎት በቃኝ ብሏል:: ይህ transition ለዳይ ማንሻፍት ቀላል አልነበረም:: ዩሮ 2016 ላይ በግማሽ ፍፃሜው በፈረንሳይ ሲሰናበቱ የፊት መስመሩን ይመራው የነበረው  ማሪዮ ጎሜዝ ነበር:: ከዛ ውድድር በኃላ ግን በተለይም ጀርመን ውጤት ባጣችባቸው ውድድሮች ሁነኛ የ9 ቁጥር ተጫዋች ለረጅም ጊዜ አልነበረም:: እንደቲሞ ቨርነር አይነት ተጫዋቾች ቦታው ትልቅ ሆኖባቸው ታይቷል:: አሁን ግን በጁሊያን ናግልስማን የሚመራው ቡድን ወሳኝ አጥቂ ያገኘ ይመስላል:: የኒውካስሉ አጥቂ ኒክ ዋልተማደ ዘንድሮ ድንቅ አቋም ላይ ይገኛል:: ፕሪሚየር ሊጉን ለመላመድም ጊዜ አልፈጀበትም:: ከኃላው የሙሲዬላ እና ቨርትዝን እርዳታ የሚያገኘው ዋልተማደ ለሀገሩ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል:: 

በስተመጨረሻም ጀርመን የምትፈልገውን አጥቂ ሳታገኝ አትቀርም! 

  • Brook Genene

    Brook is a football writer who focuses on sports injuries. He has previously written on local sports for Soccer Ethiopia and Ethiopian Business Review magazine.

    Related Posts

    Diribe Welteji banned for two years

    The Court of Arbitration for Sport (CAS) has partially upheld an appeal by World Athletics against the Ethiopian National Anti-Doping Office (ETH-NADO) and middle-distance runner Diribe Welteji Kejelcha (Ethiopia). Ms…

    ጆን ቴሪ በቼልሲ ጊዜያዊ አሰልጣኝነት ምርጫ ማዘኑን ገልጿል

    የቀድሞው የቼልሲ የመሀል ተከላካይ ጆን ቴሪ ጥር ላይ በተሰናበቱት አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ምትክ የጊዜያዊ አሰልጣኝነት እድል ባለማግኘቱ ደስተኛ እንዳልሆነ ገልጿል፡፡  ጆን ቴሪ በቼልሲ አካዳሚ በበጎ ፈቃድ አሰልጣኝነት በወር ሁለት ቀን…

    You Missed

    Ethiopia Bunna appoints new chairman 

    Ethiopia Bunna appoints new chairman 

    Diribe Welteji banned for two years

    Diribe Welteji banned for two years

    ጆን ቴሪ በቼልሲ ጊዜያዊ አሰልጣኝነት ምርጫ ማዘኑን ገልጿል

    ጆን ቴሪ በቼልሲ ጊዜያዊ አሰልጣኝነት ምርጫ ማዘኑን ገልጿል

    የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አዲስ አሰልጣኝ አግኝቷል

    የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አዲስ አሰልጣኝ አግኝቷል

    ከራባት እስከ አጋዲር፡ AFCON 2025ን የሚያስተናግዱ ዘጠኝ ስታዲየሞች

    ከራባት እስከ አጋዲር፡ AFCON 2025ን የሚያስተናግዱ ዘጠኝ ስታዲየሞች

    የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ዳሰሳ

    የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ዳሰሳ