ጆኮቪች ታሪክ መስራቱን ቀጥሏል

አስደናቂው ጆኮቪች በኤቲፒ ፍፃሜ ሲነርን በማሸነፍ በውድድሩ ክብረ ወሰን የሆነ ሰባተኛ ዋንጫውን አሸንፏል።

pic via Getty Images

የዓለማችን ቁጥር አንድ ተጨዋች ኖቫክ ጆኮቪች ግሩም በሆነ እንቅስቃሴ በቱሪን ደጋፊዎች ዘንድ ተወዳጅ የሆነውን ጣልያናዊው ያኒክ ሲነርን 6-3፣ 6-3 በማሸነፍ የኒቶ ኤቲፒ ፍፃሜ ዋንጫን እሑድ ዕለት አሸንፏል።

በዚህም ድል የ36 ዓመቱ ሰርቢያዊ ኮከብ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ላይ የሚካሀድ ውድድር ላይ በታሪካቸው ብቸኛ የሚያደርገውን እናም ክብረ ወሰን የሆነ ሰባተኛ ዋንጫ ሲያነሳ ነው። ይህንን ለማድረግ 9 የፍፃሜ ጨዋታዎችን ብቻ ነው የተጫወተው። በእሑዱ ድል ሌላኛውን ታሪካዊ ተጫዋች ሮጀር ፌደረርን ነው ማለፍ የቻለው። ሮጀር በኤቲፒ ፍፃሜ 10 ጊዜ በመድረስ ለጊዜው ያንን ክብር የወሰደበት የለም።

ኖቫክ ከጣልያናዊው ጋር ባደረግው የፍፃሜ ጨዋታ 91 በመቶ የመጀመሪያ ሰርቩን ማሸነፍ ችሏል። አንድ ሰዓት ከ 43 ደቂቃ በፈጀው ጨዋታ ጆኮቪች ካገኛቸው 8 ጊዜ የመስበር ዕድሎች ሦስቱን በመውሰድ እና ኹለቴ የመሰበር ዕድሉን በማክሸፍ ጥንካሬውን ዐሳይቷል።

አስደናቂ ሰርቭ እና እንከን የለሽ የአጨዋወት ሁኔታው ቱር ደረጃ 98ኛ ዋንጫውን እንዲያሸንፍ ረድቶታል፤ በ2023 ዓመት ደግሞ ሰባተኛ ዋንጫውን አሸንፏል። እሑድ ዕለት ያስመዘገበው ድልም በኤቲፒ ፍፃሜ ታሪኩ 50ኛው ድሉ ነበር።

“በጣም፣ በጣም ልዩ። በህይወቴ ካሳለፍኳቸው ምርጥ የውድድር ዓመታት አንዱ እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለኝም” ሲል ኖቫክ ተናግሯል። “በዚህ ሳምንት አስደናቂ ቴኒስ የተጫወተው እና ከትውልድ ከተማው ጀግና ያኒክን በማሸነፍ ውድድሩን ማሸነፌ አስደናቂ ነው። ባለፉት ሁለት ቀናት ከአልካራዝ እና ሲነር ጋር ባሳየሁት ብቃት በጣም ኮርቼያለሁ፤ ምናልባትም በአሁኑ ጊዜ ከእኔ እና ከሜድቬዴቭ ቀጥሎ ካሉት የዓለም ምርጥ ሁለት ተጫዋቾች ናቸው። እናም እነሱ እየተጫወቱበት ካለው ደረጃ አንፃር፣ እኔም ብቃቴን ከፍ ማድረግ ነበረብኝ። ግጥሚያዎቹን ማሸነፍ ነበረብኝ እና ድሉን እስኪሰጡኝ ድረስ መጠበቅ አልነበረብኝም እና ያንን ነው ያደረግኩት። በምድብ ደረጃ ከያኒክ ጋር ካደረግኹት በተለየ ስልት የተጫወትኩ ይመስለኛል፣ እና በአጠቃላይ ሳምንቱ አስደናቂ ነበር።”

የጨዋታው ቁጥሮች በአጭሩ ይኽንን ይመስላሉ: ኤስስ (13-8)፣ ድርብ ስህተት/ደብል ፎልትስ (0-1)፣ ዊነርስ (16-17)፣ ያልተገደበ ስህተት/አንፎርስድ ኤረርስ (10-30) እና ያሸነፉት አጠቃላይ ነጥብ (72-48)።

2023 ለኖቫክ አስደናቂ የውድድር ዘመን ነበር። በዚህ ሳምንትም ታሪካዊ የሆነ የዓለማችን ቁጥር አንድ በመሆን 400ኛ ሳምንቱን ሰኞ ዕለት ይዟል። ይኽንንም ያደረገ በወንድም፣ በሴትም የመጀመሪያው ተጨዋች ነው። ኤቲፒ ፍፃሜ ካሸነፈ በኋላ ቢያንስ 409 ሳምንት ድረስ ይኼዳል፤ በአውስትራሊያ ኦፕን አንደኛ እንደሚኾን ተረጋግጧል።

በሌላም በኩል ኖቫክ የኤቲፒ የዓመቱ ፍፃሜ አንደኛ ተጨዋች በመኾን ተሸልሟል። ይኽንን ክብር ሲያገኝ ለስምንተኛ ጊዜ ሲኾን በዚኽም ኺደት ከላይ ብቻውን ነው የሚገኘው።

“ለእኔ ትልቅ ትርጉም አለው” ይላል ጆኮቪች። “በሜዳው ላይ ብዙ ስሜቶች እንዳሉ ማየት ትችላለኽ። ይሰማኝ ነበር። የዛሬውን ምሽት ጨዋታ (በኤቲፒ ፍፃሜ መክፈቻ ከሆልገር ሩን ጋር ያደረገው) ለማሸነፍ በጣም ጓጉቼ ነበር ይኽንን ጫና ከጀርባዬ ላይ ለማስወገድ። ፓሪስን አሸንፌአለሁ፣ ይህም በደረጃ የተሻለ ቦታ ላይ እንድገኝ አድርጎኛል፣ እና ወደ ቱሪን ስመጣ አውቅ ነበር ማሸነፍ የሚያስፈልገኝ አንድ ጨዋታ ብቻ እንደነበር። አንድ ትልቅ ግብ ተሳክቷል፣ ሌላው ሁሉ አሁን ተጨማሪ ነው።”

የኤቲፒ ሊቀ መንበር አንድሪያ ጋውደንዚ: “የዓመቱ መጨረሻ ቁጥር 1 መሆን የማይታመን ስኬት ነው። ስምንት ጊዜ ማሳካት በጣም ያልተለመደ ነው። ኖቫክ በቴኒስ መስፈርቱን ማሳደጉን ቀጥሏል፣ እና ፍላጎቱ እና ተነሳሽነቱ እውነተኛ ሻምፒዮን ያደርገዋል። በጉዞው ውስጥ ብዙ ታላቅነት እና ክብረ ወሰን እንደሚጠብቀው ምንም ጥርጥር የለውም።”

ለአብዛኛው የቴኒስ ተጨዋች የውድድር ዓመቱ ቢያበቃም ለኖሌ ግን አንድ ወሳኝ ውድድር ይቀረዋል። በስፔን ማላጋ የሚካኼደው የ2023 ዴቪስ ካፕ ፍፃሜ 8። ከኖቬምበር 21-26 የሚካኼደው ይኽ ውድድር 8 ሀገራት የሚሳተፉበት ሲኾን የኖሌ ሀገር ሰርቢያ ግሬት ብሪቴንን በጥሎ ማለፍ ደረጃ ላይ ትገጥማለች። አሸናፊው ሀገር ወደ ግማሽ ፍፃሜ አልፎ የጣልያንን እና ኖዘርላንድስ አሸናፊ ጋር ይገናኛል።

Melaku Habtu

Related Posts

St. George wins the City Cup 

Ethiopia’s oldest and most successful club St. George have added another trophy to their cabinet by winning the 19th edition of the Addis Ababa City Cup. This is the club’s…

ሐዊ የቺካጎ ማራቶንን አሸነፈች

© Getty Images ኢትዮጵያዊቷ ሐዊ ፈይሳ በባንክ ኦፍ አሜሪካ ቺካጎ ማራቶን ባለድል ሆናለች። መገርቱ አለሙ ደግሞ በሁለተኛነት አጠናቅቃለች። ሐዊ ውድድሩን ያሸነፈችበት ጊዜ 2:14:56 ሲሆን የግሏ ምርጥ ሰዓት ነው።  የዓለም ማራቶን ሜጀር…

Leave a Reply

You Missed

St. George wins the City Cup 

St. George wins the City Cup 

ሐዊ የቺካጎ ማራቶንን አሸነፈች

ሐዊ የቺካጎ ማራቶንን አሸነፈች

Great Ethiopian Run Winners to Receive Record Prize Money

Great Ethiopian Run Winners to Receive Record Prize Money

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለአትሌቶች ከፍተኛውን ሽልማት ሊያበረክት ነው

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለአትሌቶች ከፍተኛውን ሽልማት ሊያበረክት ነው

Ethiopia’s Shure Demise Seeks Third Victory at TCS Toronto Waterfront Marathon

Ethiopia’s Shure Demise Seeks Third Victory at TCS Toronto Waterfront Marathon

የ2025 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ተሸላሚዎች ይፋ ሆኑ

የ2025 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ተሸላሚዎች ይፋ ሆኑ