
እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ትውልዳቸው ከኢትዮጵያ የሚመዘዝ ተጫዋቾችን ለብሔራዊ ቡድን እንዲጫወቱ ጥረት ማድረግ ከጀመረ ቆይቷል:: ለዚህም ይረዳው ዘንድ ከ “አማካሪ/ጉዳይ አስፈፃሚ” ጋር ለመስራት መስማማቱ ይታወሳል:: አማካሪው ሌሎች ስራዎችንም እንደሚሰራ ልብ ይሏል:: የሀገሪቱ የዜግነት መመሪያ እንዲሻሻልም ፌዴሬሽኑ እየጣረ ነው::
የብሔራዊ ቡድኑ የአሜሪካ ጉዞ “50,000 ዶላር” ከማግኘት ባለፈ ይህንን የፌዴሬሽኑን እቅድ ለማስፈፀም ዘር የሚዘራበት ዕድል አለው::
ከዲሲ ዩናይትድ ጋር ከመጫወት ባለፈ ቡድኑ ጨዋታውን በሚያደርግበት አካባቢ በአካዳሚዎች: በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በኮሌጆች እየተጫወቱ ከሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ታዳጊዎች እና ወጣቶች ጋር ልምምድ በመስራት እና የድብልቅ ጨዋታ በማድረግ ማልያውን መልበስ ያለውን ስሜት ማሳየት ይችላል:: ዋልያዎቹ የአንድ ለአንድ ስልጠና ለታዳጊዎቹ ሊሰጡም ይችላሉ:: ይህ ታዳጊዎቹ ነገ ለብሔራዊ ቡድኑ ለመጫወት ፍላጎት እንዲያድርባቸው ሊያደርግ ይችላል::