በታላላቆቹ የአውሮፓ ሊጎች ግቦችን እያመረቱ ያሉ አምስት ተጫዋቾች

በዘንድሮው የውድድር ዘመን በአምስቱ ታላላቅ የአውሮፓ ሊጎች ከዚህ በፊት በግብ አስቆጣሪነታቸው የሚታወቁት ተጫዋቾች አሁንም ግብ ማምረታቸውን ቀጥለውበታል፡፡ እንደሀሪ ኬን ፤ አርሊንግ ሀላንድ እና ኪሊያን ምባፔ ያሉ ተጫዋቾች በርካታ ግቦችን በማስቆጠር ግንባር ቀደም ናቸው፡፡

እንደስፖርቲንግ ፔዲያ ዘገባ ከሆነ ደግሞ የሞናኮው የፊት መስመር ተጫዋች አንሱ ፋቲ በወጥነት እንደዚሁም እድሎችን በመጠቀም አንጻር በአውሮፓ ያሉትን ታላላቅ አጥቂዎች እንደሚበልጣቸው ቁጥራዊ መረጃዎችን አስደግፎ አቅርቧል፡፡

አንሱ ፋቲ በተሰለፈባቸው ሁሉም የሞናኮ ጨዋታዎች ግቦችን ማስቆጠር ችሏል፡፡ በ3 የሊግ ጨዋታዎች 5 ግቦች አሉት፡፡  ይህም በየ32 ደቂቃው ግቦችን እንደሚያስቆጥር ማሳያ ነው፡፡ ፋቲ ምንም እንኳን ለረጅም ጊዜ በጉዳት ርቆ የቆየ ቢሆንም ወዲያውኑ ወደግብ ማግባቱ መመለስ ችሏል፡፡ እንደአንሱ ፋቲ በተሰለፈባቸው ጨዋታዎች ሁሉ ግብ ማስቆጠር የቻለው ሀሪ ኬን ሲሆን በየ45 ደቂቃው ግብ እንደሚያስቆጥር ለማወቅ ተችሏል፡፡

ሀላንድ ግቦችን በየ66 ደቂቃ የሚያስቆጥር ሲሆን ምባፔ በበኩሉ በየ72 ደቂቃው ግቦችን ያስቆጥራል፡፡

የአይንትራክት ፍራንክፈርቱ ወጣት ተጫዋች ካን ኡዙን በተሰለፈባቸው 80% ጨዋታዎች ግቦችን ማስቆጠር ችሏል፡፡

ሀላንድን የሚጠጋ ሪከርድ በፕሪሚየር ሊጉ ያለው የቦርንማውዙ አጥቂ አንትዎን ሴሜንዮ ሲሆን በተሰለፈባቸው 57% ጨዋታዎች ግቦችን አስቆጥሯል፡፡

Brook Genene

Brook is a football writer who focuses on sports injuries. He has previously written on local sports for Soccer Ethiopia and Ethiopian Business Review magazine.

Related Posts

የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ዳሰሳ

በበረከት ጸጋዬ 35ተኛው የአፍሪካ ዋንጫ (ከታህሳስ 21 እስከ ጥር 10/2018) በሞሮኮ የሚካሄድ ሲሆን የወቅቱ ሻምፒዮን አይቮሪኮስት :ደቡብ አፍሪካ እና መሰል ሀገራት ከሚቀጥለው አመት የፊፋ የአለም ዋንጫ ቀደም ብለው በአህጉራዊ ውድድሩ…

ሞ ሳላህ ላይ እየተሰጡ ያሉ ትችቶች እንዴት ይታያሉ? 

ግብጻዊው የሊቨርፑል የፊት መስመር ተጫዋች ሞ ሳላህ ከሊዲሱ ጨዋታ መልስ በሰጠው አስተያየት መነጋገሪያ ሆኖ ከርሟል፡፡  “ 90 ደቂቃ ሙሉ ተጠባባቂ ወንበር ላይ መሆኔን ላምን አልችልም፡፡ ለሶስተኛ ተከታታይ ጨዋታ ነው ይህ…

You Missed

የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ዳሰሳ

የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ዳሰሳ

ሞ ሳላህ ላይ እየተሰጡ ያሉ ትችቶች እንዴት ይታያሉ? 

ሞ ሳላህ ላይ እየተሰጡ ያሉ ትችቶች እንዴት ይታያሉ? 

ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች

ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች

Qatar to build 11 running tracks in 11 countries

Qatar to build 11 running tracks in 11 countries

በአፍሪካ ትምህርት ቤቶች የእግር ኳስ ሻምፕዮና የሴካፋ ማጣሪያ ኢትዮጵያ በሁለቱም ጾታ ለፍጻሜ አለፈች

በአፍሪካ ትምህርት ቤቶች የእግር ኳስ ሻምፕዮና የሴካፋ ማጣሪያ ኢትዮጵያ በሁለቱም ጾታ ለፍጻሜ አለፈች

ቀይ ቀበሮዎቹ ካታር ለመገኘት በሞሮኮ ይፋለማሉ

ቀይ ቀበሮዎቹ ካታር ለመገኘት በሞሮኮ ይፋለማሉ