አትዮጵያ በገብረመድህን ኃይሌ ስር የምታደርገው የመጀመሪያው ጨዋታ ይሆናል::
ለ2026 አለም ዋንጫ በሚደረገው ማጣሪያ ኢትዮጵያ ሴራሊዮንን ምሽት 4 ሰዓት ላይ በኤል-አብዲ ስቴዲየምትገጥማለች::

ኢትዮጵያ የአለም ዋንጫ ማጣሪያዋን ሴራሊዮንን በመግጠም ትጀምራለች::
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በአዲሱ አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሃይሌ እየተመራ የመጀመሪያውን የነጥብ ጨዋታያደርጋል::
ከጅማ አባ ጅፋር እና መቀለ 70 አንደርታ ጋር የፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ መሆን የቻሉት እና ኢትዮጵያ መድንከመጡም በኃላ የተሳካ ቆይታን ያደረጉት አሰልጣኝ ገብረመድን ከውጤት ከራቀ ሰንበትበት ያለውን ብሄራዊቡድን የማንሰራራት ከፍተኛ ኃላፊነት አለባቸው::
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ደካማ እንቅስቃሴ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን ከምድቡምበ4 ነጥብ መጨረሻ በመሆን ነበር ያጠናቀቀው::
ብሄራዊ ቡድኑ በሰኔ 2022 ግብፅ ላይ ካስመዘገበው ድንቅ ብቃት መልስ በቻን ውድድርም ሆነ በማጣሪያጨዋታዎች ደካማ እንቅስቃሴን አሳይቷል:: ይህም ለአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከኮንትራታቸው መጠናቀቅ ቀደምብሎ ከስራ ለመልቀቅ ምክንያት ሆኗል::
የውበቱ ቡድን ኳስን አዘውትሮ የመቆጣጠር ልምድ ቢኖረውም አደገኛ ክልል ውስጥ ከመገኘት እና እድሎችንከመፍጠር አንፃር ብዙ ጥያቄዎች የሚነሱበት ነበር:: ገብረመድህን በቅድመ ጨዋታ መግለጫቸው ” በራሳችንሜዳ ብዙ የመቆየት ነገር አይኖርም ” በማለት መናገራቸው የተለየ ነገርን ይዘው ለመምጣት እንዳሰቡ ፍንጭንየሰጠ ነበር::
“ከኳስ ውጭ ያለን እንቅስቃሴ በጣም ደካማ ነው ፤ ይሄንንም ለማሻሻል በጣም እየሰራን ነው። ሁሌም ቢሆንኳስ ስናጣ ሁላችንም መሮጥ ይኖርብናል:: ከዚህ አንፃር መጠነኛ ለውጦች ቢኖርም ይበልጥ በጊዜ ሂደት ግፊትአሳድረን የምንሰራበት ከሆነ ሊመጣ ይችላል” በማለትም ምን ላይ አተኩረው ልምምዳቸውን እንደተገበሩገልፀዋል::
ዋልያዎቹ የወሳኝ አጥቂዎቻቸውን ግልጋሎት አያገኙም:: ሽመልስ በቀለ እንደዚሁም ለረጅም ጊዜ ጉዳት ላይየከረመው አቡበከር ናስር አይጫወቱም:: ከዚህ ቀደም እራሱን ከብሄራዊ ቡድን ያገለለው ጌታነህ ከበደበውሳኔው መፅናቱን ለማወቅ ተችሏል::
የባህር ዳሩ አማካይ አለልኝ አዘነ ከቡድኑ ጋር አለመኖር በብዙዎች ዘንድ ጥያቄን ያስነሳ ነበር:: በእርሱ ቦታ ላይያሉት ጋቶች ፓኖም እና ናትናኤል ዘለቀ የተሻለ ብቃት ላይ በመኖራቸው መመረጣቸውን ገብረመድህንተናግረዋል::
ተጋጣሚው ቡድን ሴራሊዮን እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ አልቻሉም:: ለዚህ ጨዋታ ባደረጉትዝግጅት ከቤኒን ጋር አቻ ሲወጡ ሱማሊያን አሸንፈዋል::
ሴራሊዮን በአዲሱ አሰልጣኝ አሚዱ ካሪም እየተመራች ትቀርባለች:: ካሪም ከኢትዮጵያ ከባድ ፉክክርእንደሚጠብቁ እና ተጋጣሚያቸው በቀላሉ እጅ እንደማትሰጥ ተናግረዋል::







