
ብዙ ጊዜ የlow-block ቡድኖች እየተባለ ሲነገር ይሰማል:: የዚህ አጨዋወት ዋና አላማ መከላከልን ቅድሚያ የሰጠ ለማለት እንደሆነ ግልፅ ነው::
ግን low block ለተወሰኑ ቡድኖች ብቻ የሚሰጥ ባህሪይ ነው?
ከኳስ ውጪ ያሉ አደረጃጀቶች እንደቡድን በግርድፉ በ 3 ይከፈላሉ::
High block(High press) ባላጋራን ከግብ ክልሉ ብዙም እንቅስቃሴውን ሳያሳድግ ከተቻለ ነጥቆ የግብ እድልን መፍጠር ወይም የ build up እቅዱን ማበላሸት ነው::
Medium block ደግሞ ተጋጣሚን ከተከላካይ ወደ አማካይ (ሁለተኛው ሜዳ) የሚደረጉ ኳሶችን ማቋረጥ እና መልሶ ወደ ግብ እድል መፍጠር ነው::
በ medium block ወቅት ተጋጣሚ ቡድን በመሃል ተከላካዮች ኳስን ወዲህ- ወድያ እያደረገ ቢቀባበልም ተከላካዩ ቡድን ወደ ሁለተኛው ሜዳ የሚላከውን ኳስ በትዕግስት ሲጠብቅ ይስተዋላል::
Low-block በቀላል ቋንቋ የመጨረሻውን ተሻጋሪ ኳስ ወይም assist ሊሆን የሚችለውን ገዳይ ፓስ መከላከል ነው:: ሳጥንን መከላከል ተብሎም ሊጠራ ይችላል::
እነዚህ የመከላከል አደረጃጀቶች የትኛውም ቡድን በአንድ ጨዋታ ክፍለ ጊዜ በየትኛውም ሰዓት እንደአስፈላጊነቱ ሊተገብራቸው የሚችላቸው ናቸው:: እንደአስፈላጊነቱ የሚለው ይሰመርበት::
በ2023/24 የውድድር ዘመን ማንቸስተር ሲቲ በ high press የተጋጣሚ የመጀመርያው ሦስተኛ ሜዳን ክፍል ከ አስር ሦስት ኳሶችን በአማካይ መልሶ ተቆጣጥሯል/አበላሽቷል:: የተቀሩትን ሰባት በ Medium አልያም Low block ነው የተከላከለው ማለት ነው::
ይህንን ቡድን high block የሚከላከል ቡድን ብሎ መጥራት ጥያቄ የሚያስነሳው ለዚህ ነው:: እውነት ነው ሜዳ ውስጥ የት ኳሱን መንጠቅ እንደሚፈልጉ እና ተነሳሽነታቸው ግልፅ ነው ግን በ medium እና low blockም አሳምረው ይከላከላሉ::
ስለዚህ… ሦስቱ የመከላከል አደረጃጀቶች ቡድኖችን የምንለያይበት ማንነቶች ሳይሆን ሁሉም ቡድኖች ይብዛም ይነስ እንደየአስፈላጊነቱ የሚተገብሯቸው ናቸው::
ደጋፊ ምስል- ትላንት ባርሴሎና በአንድ ሰው ቁጥር ብልጫ እና አራት ለ ምንም እየመራ በ low block የሚከላከልበት አደረጃጀት ነው::
