
የስፔን የክለብ እግርኳስ ታላቁ ፍልሚያ ተደርጓል። በሊጉ የዋንጫ ፉክክር አሸናፊውን ይጠቁማል ተብሎ የተጠበቀው ጨዋታ በ ባርሴሎና የበላይነት ተደምድሟል።
ብዙ ክስተቶችን ባስተናገደው ይህ ጨዋታ የ ሬያል ማድሪድን ታክቲካዊ አቀራረብ እና በጨዋታ መኅል የተገበሯቸውን In game managements ውጤቱ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድረዋል። ይህም ታክቲካዊ ትንታኔ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል።
በዘጠኝ ነጥብ ልዩነት በባርሳ ተበልጠው ወደዚህ ጨዋታ የቀረቡት ሬያሎች ማሸነፍን እንደ ብቸኛ አማራጭ ይዘው ቀርበዋል። ይህም አሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ ከመረጧቸው የመጀመሪያ11 መመልከት ይቻላል። የአማካይ ክፍሉ እምብርት ላይ ካማቪንጋ ከ ችዋሜኒ ቅድሚያውን አግኝቷል። በፈጣን ሩጫውዎቹ እና ከርቀት ወደጎል የመሞከር አቅሙ ካማቪንጋ ይታወቃል። በሊቨርፑሉ የመልስ ጨዋታም ብዙ አድና ቆትን አትርፏል።
የቾዋሜኒ አለመሰለፍ የሬያል ማድሪድ ጨዋታን የመቆጣጠር አቅም ቢቀንሰውም። ካርሎ አንቸሎቲ ካማቪንጋን ለማሰለፍ መወሰናቸው ትክክለኛነት በ ሬያል ማድሪ ብቸኛ ግብ ላይ ተስተውሏል።

የናቾን በግራው መስመር መነጠል እና የቪኒን ወደሳጥን መግባት ያስተዋለው ካማቪንጋ በፍጥነት አንድ የመስመር አጥቂ የሚያደርገውን ሩጫ በማድረግ የ ናቾን መስመር ሰንጣቂ ኳስ ተቀብሎ ማትቃቱን አስቀጥሏል። ይህ እንቅስቃሴ ለጎሉ በቀጥተኝነት ምክንያት ባይሆንም። ጫናው አራውሆ እራሱ ላይ እንዲያስቆትር አስገድዶታል
ለጎሉ መገኘት እና በሬያል መልሶ ማትቃቶች ላይ ካማቪንጋ ጥሩ አስተዋፅኣ ቢኖረውም። በወሳኙ የተከላካይ አማካይነት ሚና ላይ ክፍተቶች ታይተውበታል።

በምስሉ እንደሚታየው ካማቪንጋ ዙሪያውን በመቃኘት አደጋውን ማንበብ እና ሁለተኛ ኳስን ለማግኘት የተዘጋጀውን ሰርጂ ሮቤርቶ መጫን ይገባው ነበር። አቋቋሙም የተወሰኑ ሚትሮች ወዳ መኅል መሆን ይገባው ነበር። ሰርጂ ሮቤርቶ ይሄን የግብ እድል ለጥቂት ነበር የሳተው።
ሌላው የሬያል ማድሪድ የጨዋታ አቀራረብ ላይ ከተለመደው ውጪ ሆኖ የተስተዋለው የ ፌዴ ቫልቬርዴ የሜዳ ላይ ሚና ነበር። በፈጣን የሽግግር ማጥቃት ወቅት ከኳስ ጋር ሩጫዎቹ እና የተጋጣሚን መልሶ ማጥቃት መከላከል ላይ የ ቀኝ መስመሩ ደጅን የሆነው ኡራግዋዊ በዚህ ጨዋታ የመከላከል ሚናው ተገድቦ ተስተውሏል። ይህም ለባርሳ በርካታ የማጥቃት አጋጣሚዎችን ፈጥሯል።

ይህ በጨዋታው የመጀመርያ ደቂቃዎች ላይ ሬያሎች ከራሳቸው የግብ ክልል ለመውጣት እየመሰረቱ ያሉበት ወቅት ነው። የኋላ መስመሩ ወደቀኝ ተስቦ ይታያል። ኤደር ሚሊታኦ ከተፈጥሯዊው ቦታው እጅግ እርቆ ሲገኝ ፣ ፌዴ ቫልቨርዴ በምስሉ ላይ አይታይም።

በቁጥር ብልጫ ተጭነው የነበሩት ባርሳዎች ኳስን አስጥለው ቡስኬትስ እግር ስር ኳስ ስትገባ፣ ሬያሎች ከቅርፅ ውጪ ሆነው ይታያሉ። ኤዴር ሚሊታኦ(በነጭ የተከበበው) ከሳጥን ውጪ ይገኛል። የእርሱን ቦታ ለመሸፈን ሩዲገር ወደ ሌቫንዶውስኪ ይጠጋል። ይህም ለ ራፊንያ ሰፊ ቦታን ይፈትራል። ሜዳውን አስፍቶ ሲጠብቅ የነበረው ናቾም ከእንቅስቃሴው እሩቅ ነበር;;
ይህ በበፊት ጨዋታዎች የመከሰት እድሉ እጅግ ጠባብ ነበር። ቫልቬርዴ ሁሌም እንደ አምስተኛ ተከላካይ የቀኝ መስመሩን በመዝጋት ያገለግል ነበር። የፌዴ በቦታው መገኘትም የ ሚሊታኦን ሃላፊነት በሳጥን ውስጥ ብቻ እንዲገደብ እና ከላይ የተከሰተው አይነት አደጋ እንዳይከሰት ያደርግ ነበር።

በሌላ አጋጣሚም በፍጥነት ከተገኘ የእጅ ውርወራ ቫልቬርዴ ጥሩ አጋጣሚን መፍጠር ችሎ ነበር። ለ ሞድሪች ለማቀበል የሞከረው ኳስ በ ክሪስቸንሰን እና ቡስኬትስ ሲቋረጥ ግን በፍጥነት የሬያል ማድሪድ ጥሩ እድል ወደ ስጋት ተለወጠ። አስገራሚ ምሽትን ያሳለፈው ቡስኬትስ በ ግሩም መስመር ሰንጣቂ ኳስ ሌዋንዶቩስኪን ማግኘት ቻለ።


ሌዋንዶቭስኪ ቀናንመመልከት ቢችል እና ውሳኔው ትክክል ቢሆን ኖሮ ጋቪ እና ዲ ዮንግ በግራ መስመር በ ብቸኛው ካርቫሃል ላይ የቁጥር ብልጫን መፍጠር ለው ነበር። ቫልቬርዴ በነጭ ክብ እንደሚታየው ይሄ ኳስ ቢገለበጥ ካርቫሃልን የመርዳት እድሉ እጅግ ጠባብ ነበር;;
በሁለተኛው አጋማሽ የአማካይ ክፍልን ቁጥር ለመጨመር የወሰኑት ሬያሎች የበለጠ የመስመር የበላይነቱ እንዲወሰድባቸው አድርጓል። ምንም እንኳን የ ሬያል የሁለተኛ አጋማሽ አማካይ ዳይመንድ ቅርፅ የጨዋታው ላይ ያላቸውን ቁጥጥር ከፍ ቢያደርገውም በ ባልዴ በኩል ያለው መስመር ተደጋጋሚ ጥቃቶችን እንዲደርስባቸው ምክንያት ሆኗል።
ከልብ አንጠልጣይ 90 ደቂቃዎች በኋላ የሊጉ መሪ ባርሴሎና የዋንጫ እድሉን በሚገባ ማስፋት ችሏል። ሬያል ማድሪዶችም ውጤቱን ለማግኘት ከመጣ ጉጉት የወሰኗቸው ውሳኔዎች ዋጋ አስከፍለዋቸዋል። ሁለቱ ቡድኖች ከሁለት ሳምንታት በኋላ በንጉሱ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ሲገናኙ የሚፈጠረውን ለማየት ሁሉም በጉጉት ይጠብቃል።