Sudden Cardiac Arrest- አደገኛው ህመም በስፖርቱ አለም

በስፖርቱ አለም ከሚያጋጥሙ ድንገተኛ ህመሞች መካከል sudden cardiac arrest ይጠቀሳል:: ይህ ህመም ያለምንም ስሜት ወይም ማስጠንቀቂያ በድንገት ከመከሰቱ በተጨማሪ በአንድ ጊዜ ህይወትን አደጋ ላይ መጣሉ አሳሳቢ አድርጎታል:: ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በዚህ ህመም የተጠቁ ተጫዋቾች ቁጥር በብዛት መጨመሩ ሁኔታው ትኩረት እንዲያገኝ አድርጏል::

ከጥቂት ወራት በፊት ጋናዊው የ28 አመት ተጫዋች ራፋኤል ድዋሜና በሚጫወትበት የአልባኒያ ሊግ ሜዳ ላይ ተዝለፍልፎ በመውደቅ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል:: ድዋሜና የልብ ህመም እንዳለበት አስቀድሞ የተነገረው ቢሆንም እርሱ ግን እግር ኳስ ጨዋታ ማቆምን አልፈለገም:: ከዚህም በተጨማሪ በልቡ ውስጥ ተቀምጦ የነበረውን Intractable Cardiovertor Defibrillator (ICD) እንዲወጣ ወስኗል::

Ghanaian footballer Dwamena dies during match in Albania – Photo by anews

የድዋሜናን ሁኔታ ይከታተል የነበረው የልብ ስፔሻሊስት አንቶኒኦ አሶ ” በእርሱ ላይ የደረሰው ህመም የተጠበቀ ነው:: ከሁለት አመት በፊት የልብ ምት መዛባት አጋጥሞት ነበር:: ህይወቱም ሊተርፍ የቻለው ICD በውቅቱ ስለተገጠመለት ነበር” በማለት አስረድቷል::

ድዋሜና በዶክተሮች እና በጏደኞቹ እግር ኳስን ማቆም እንዳለበት በተደጋጋሚ ቢነገረውም አሻፈረኝ ብሏል:: 2017 ላይ ወደ ብራይተን የሚወስደውን የ 10 ሚሊዮን ፓውንድ ዝውውር የተስማማ ቢሆንም የህክምና ምርመራን ማለፍ ባለመቻሉ አማካይነት ስምምነት ላይ ሳይደርስ ቀርቷል:: በጥቅምት ወር 2021 ላይ ሜዳ ላይ በመውደቁ ምክንያትም ኮንትራቱ በጊዜ እንዲቋረጥ ሆኗል::

በእምነቱ የማይደራደረው ድዋሜና ” ልቤን የሚቆጣጠረው እግዚአብሔር ነው” በማለትም በአንድ ወቅት ተናግሯል::

ድዋሜና ይጫወትበት የነበረው ኢግናትያ ክለብ ዳይሬክተር ክሌጂ ዜኔላጅ ክለቡ ድዋሜና ላይ ክትትል ማድረጉን እና የአልባኒያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሮቶኮልን መከተሉን ተናግረዋል:: ድዋሜና ታህሳስ ወር 2022 ላይ ከመጣ በኃላም ሶስት ጊዜ የህክምና ምርመራ አድርገውለታል::

” እርሱ መጫወትን መርጧል:: ክለቡ ሁሉንም ምርመራዎች እስካደረገ ድረስም መቀጠል ይችላል:: ” በማለት ዜኔላጅ ተናግረዋል::

የድዋሜና የልብ ህመም መጀመሪያ የታወቀው 2017 ላይ በስዊስ ሱፐር ሊግ የሚጫወተውን ኤፍ ሲ ዙሪክ ከተቀላቀለ በኃላ ነው:: የክለቡ ፕሬዝዳንት አንቺሎ ካኔፓ ” ሁልጊዜም አዲስ ተጫዋች ከማስፈረማችን በፊት የህክምና ምርመራ እናደርጋለን:: የልብ ምት ችግሮችን ራፋኤል ላይ አስተውለን ነበር:: ከተጫዋቹም ጋር ሆነ ከሌሎች ስፔሻሊስቶች ጋር ስለ ጉዳዩ ተወያይተን ነበር:: ከምርመራዎቹ በኃላ በእንቅስቃሴው መቀጠል እንደሚችል ነው ሀኪሞቹ የነገሩን::”

ዙሪክ ተንቀሳቃሽ የሆነ ዲፊብሪሌተር በየጨዋታቸው ያስቀምጡ ነበር:: ነገር ግን በስዊዘርላንድ ቆይታው ምንም አይነት የልብ ህመም አላጋጠመውም:: ካሳየው ድንቅ ብቃት የተነሳም ለጋና ብሄራዊ ቡድን ተመርጧል::

ካኔፓ በአስተያየታቸው ድዋሜና ጥሩ ተጫዋች ብቻ ሳይሆን መልካም ባህሪ እንዳለው መስክረዋል::

2018 ላይ ወደ ስፔን ላሊጋ በማምራት ሌቫንቴን ተቀላቅሏል:: ከዚህም በኃላ በውሰት ወደ ሪያል ዛራጎዛ አምርቷል:: እዛም በነበረበት ወቅት የልብ ችግር እንዳለበት ተነግሮታል:: የልብ ምቱም ፈጣን እና የተዛባ መሆኑ ተረጋግጧል::

አልቤርቶ ዞሮ የተባለው የቀድሞው የሪያል ዛራጎዛ ተጫዋች ” ጠንካራ ተጫዋች እና ብዙ ኃይል ያለው ነበር:: ዝምተኛ ነበር ግን ደግሞ ሳቂታም ነበር:: ሜዳ ላይ ደግሞ ለቡድኑ የሚታትር ተጫዋች ነበር:: ስለህመሙ እናውቅ ነበር:: አንድ ጨዋታ ላይ እረፍት ስንወጣ ህመም ስሜት ተሰምቶት ነበር:: ምርመራ ከተደረገ በኃላም ለተወሰነ ጊዜ ከሜዳ እንደሚርቅ ተነግሮናል::” በማለት ሁኔታውን ገልፆል::

ድዋሜና ጥር 2020 ላይ ICD ልቡ ውስጥ እንዲቀመጥ ተደርጎ ነበር:: ዲፍብሪሌተር ማስገባት የመጀመሪያ ህክምና እንደሆነ እና ደጋግሞ ህመሙ የሚከሰት ከሆነ በደም ስሮቹ ውስጥ ቱቦ በማሳለፍ ህክምና ሊያስፈልገው እንደሚችል ተነግሮት ነበር:: እሱ ግን የተቀበለው ዲፍብሪሌተሩን ብቻ ነበር:: ከዛ በኃላ ወደ ዴንማርክ ያመራው ድዋሜና የልብ ህመሙ በተደጋጋሚ ስላስቸገረው ክለቡ ኮንትራቱን አቋርጦበት ወደ አልባኒያ አምርቷል:: እዛም ህይወቱ አልፏል::

የዊጋን አትሌቲክ አጥቂ የሆነው ቻርሊ ዋይክ ህዳር ወር 2021 ላይ ራሱ የመዞር ስሜት እና ያንን ተከትሎ ሜዳ ላይ መውደቅ ሲያጋጥመው አሰልጣኙ ሊያም ሪቻርድሰን ነበር ሲ ፒ አር በመስራት ንቃቱን መልሶ እንዲያገኝ ያደረገው::

Wyke’s device is under his arm and snakes across his chest, clearly visible through the skin. ‘I always feel my arms trying to protect it,’ he said about adjusting his game. Bernard Platt / Wigan Athletic

ከጥቂት ወራት በኃላ መጋቢት ላይ ሌላ ችግር አጋጠመው:: ትንሽ ሰዎች ብቻ ነበሩ በድጋሚ ሜዳ ላይ ይመለሳል ብለው ያሰቡት::

በ2020-21 የውድድር ዘመን ለሰንደርላንድ 31 ግቦችን ማስቆጠር የቻለው አጥቂ ደረቱ ውስጥ ከተቀበረው ዲፊብርሌተር ጋር ሆኖ ብቃቱን ለማስቀጠል መጣሩን ቀጠለ:: ዲፊብርሌተሩ ከሞኒተር ጋር የተገናኘ ሲሆን በብሉቱዝ የልቡን ሁኔታ ወደ ልብ ሃኪሙ ስልክ ይልካል::

በልብ ህመም ምክንያት ከእግር ኳሱ አለም የተገለለው ፋብሪስ ሙአምባ ለዋይክ ተመልሶ መምጣት ጥሩ ውሳኔ ላይሆን እንደሚችል መክሮት ነበር::

ቤተሰቡ ላይ ትኩረት እንዲያደርግ ቢመከርም ወደ እግር ኳስ መመለስን ግን እንደትክክለኛ ውሳኔ ወስዶታል::

በአጠቃላይ ስድስት የቀዶ ህክምና ተደርጎለታል:: በሚጫወትበት ወቅትም ደረቱን የሚሸፍን መከላከያ ያደርጋል::

በቅርቡ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሉተን ታውን ከቦርንማውዝ ባደረጉት ጨዋታ ቶም ሎክየር የተባለው የ29 አመት ተጫዋች በድንገት ሜዳ ላይ ይወድቃል:: ብዙዎችን ባስደነገጠው በዚህ ክስተት በቶሎ እርዳታን እንዲያገኝ በመደረጉ ምክንያት ህይወቱ ሊተርፍ ችሏል:: ሎክየር እንደዚህ አይነት ችግር ሲያጋጥመው ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው:: ሉተን በሻምፒየንሺፕ ባደረጉት ጨዋታም በተመሳሳይ መውደቁ ይታወቃል::

ሎክየር ሆስፒታል ከተወሰደ በኃላ በድጋሚ እንደዚህ አይነት ችግር እንዳያጋጥመው ICD ተደርጎለታል:: በሆስፒታል ምርመራ እና ጥብቅ ክትትል ከተደረገለት በኃላ ወደ ቤቱ ሄዶ እንዲያገግም ተደርጏል::

ክለቡም የሎክየርን ህይወት ለማትረፍ ትብብር ያደረጉትን የጤና ባለሙያዎች በሙሉ አመስግኗል:: ደጋፊውም ላስተላለፉት መልካም መልዕክት ምስጋና ቀርቦላቸዋል::

የልብ ድካም ( Sudden Cardiac Arrest) እንዳያጋጥም ቅድመ ምርመራዎች ( Screening) የሚያስፈልግ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ህመሙ ካጋጠመ በኋላ የሚደረጉ እርዳታዎች ማለትም Cardiopulmonary Resuscitation ( CPR) እና Automated External Defibrillator ( AED) ህይወትን ከማትረፍ በኩል ያላቸው ሚና ላቅ ያለ ነው፡፡

እንደዚህ ያለው ህመም በአብዛኛው ጊዜ በእንቅስቃሴ ወቅት የሚያጋጥም ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ የልብ ምት መዛባት (arrythmia) የሚያጋጥመው በዚህን ወቀት በመሆኑ ነው፡፡ የድንገተኛ የልብ ህመም መንስኤ የልብ መዋቅራዊ (structural) እና ኤሌክትሪካዊ መስተጋብር ላይ በሚኖር ችግር አልያም መዛባት ምክንያት ነው፡፡

ከ60-80 % የሚሆኑ ድንገተኛ የልብ ህመም የሚያጋጥማቸው ተጫዋቾች ከህመሙ መከሰት በፊት ምንምአይነት ምልክት የማያሳዩ ናቸው፡፡ ነገር ግን በቀሪዎቹ ላይ የሚከተሉት ምልክቶች ይስተዋላሉ፡- ድንገተኛ ራስንመሳት፤ በእንቅስቃሴ ላይ የሚያጋጥም የደረት ህመም፤ ምክንያቱ ያልታወቀ የሰውነት መንቀጥቀጥ፤ የትንፋሽማጠር እና በቶሎ መድከም ናቸው፡፡

ድንገተኛ የልብ መድከም በሚያጋጥመበት ወቅት በቶሎ ምላሽን ለመስጠት መመሪያዎችን ያቀፈ ጽሁፍበልምምድ ቦታዎችም ሆነ ውድድር በሚደረግባቸው ስፍራዎች ሊዘጋጁ ያስፈልጋል፡፡ እነዚህ የድንገተኛ ምላሽመመሪያዎች የተለያዩ ነገሮችን በውስጣቸው ያቀፉ ናቸው፡፡ ከእነዚህም መካከል ለህክምና አባላቱ ቀጣይነትያለው ስልጠና መስጠት ፤ በአጭር ደቂቃ ውስጥ መሳሪያዎችን ( Defibrillator) የመጠቀም ክህሎት ፤ ወደህክምና ስፍራ በቶሎ ተጫዋቾችን መውሰድ እና የመሳሰሉት ተካተውበታል፡፡

በአጠቃላይ ከልብ ህመም ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ አደጋዎች በቂ ዝግጅት ካለማድረግ እና የሰለጠኑባለሙያዎችን ካለመያዝ ጋር የሚገናኙበት ሁኔታ አለ፡፡ ስለዚህ ከዚህ ጋር በተያያዘ በሁሉም እርከን የሚገኙክለቦች ለእንደዚህ ላሉ ችግሮች ብቁ ሆነው መዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡

በሀገራችን ከልብ ህመም ጋር ተያይዞ ከበድ ያሉ ጉዳቶች ብሎም ሞት እንዳያጋጥም ፌደሬሽን ፤ ክለቦችናእያንዳንዱ የሚመለከተው አካል በህብረት እና በትኩረት መስራት ይኖርባቸዋል፡፡ ውድድር በሚደረግባቸውቦታዎች የልብ እርዳታ የሚሰጥባቸው ማሽኖች እና ስልጠና የወሰዱ ብቁ ባለሙያዎች ሊኖሩ ያስፈልጋሉ፡፡

Brook Genene

Brook is a football writer who focuses on sports injuries. He has previously written on local sports for Soccer Ethiopia and Ethiopian Business Review magazine. He also has over a decade of experience covering the Bundesliga and German football for several outlets.

Related Posts

በሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ዙሪያ የስፖርት ግልግል ፍርድ ቤት ምን ይላል?

ከአራት ሳምንታት በፊት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብን “የታገዱ ተጫዋቾችን በማሰለፍ” በሚል በኢትዮጵያ ዋንጫ ያገኘው ድል ተሰርዞ በፎርፌ እንዲሽነፍ እና የቀጣዩ የውድድር ዘመን የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ…

አለም አትሌቲክስ እና የሴቶች የፆታ ምርመራ ጉዳይ

ባለፈው አመት በፓሪስ በተካሄደው የኦሎምፒክ ውድድር አልጄሪያዊቷ አትሌት ኢማን ካሊፍ ከፆታ ተገቢነት አንፃር በርካታ ጥያቄዎች ሲነሱባት እንደነበር የሚታወስ ነው::  ከዚህ በመቀጠልም በሌሎች ውድድሮች ለመሳተፍ ግዴታ ምርመራ ማድረግ እንዳለባት የሚገልፁ ደንቦች…

Leave a Reply

You Missed

St. George wins the City Cup 

St. George wins the City Cup 

ሐዊ የቺካጎ ማራቶንን አሸነፈች

ሐዊ የቺካጎ ማራቶንን አሸነፈች

Great Ethiopian Run Winners to Receive Record Prize Money

Great Ethiopian Run Winners to Receive Record Prize Money

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለአትሌቶች ከፍተኛውን ሽልማት ሊያበረክት ነው

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለአትሌቶች ከፍተኛውን ሽልማት ሊያበረክት ነው

Ethiopia’s Shure Demise Seeks Third Victory at TCS Toronto Waterfront Marathon

Ethiopia’s Shure Demise Seeks Third Victory at TCS Toronto Waterfront Marathon

የ2025 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ተሸላሚዎች ይፋ ሆኑ

የ2025 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ተሸላሚዎች ይፋ ሆኑ