ሰኞ ምሽት በተካሄደ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኤቨርተን ማንችስተር ዩናይትድን 1 ለ 0 አሸንፈዋል:: በዚህ ጨዋታ ትኩረት የሳበው ክስተት የኢድሪሳ ጋና ጌይ ቀይ ካርድ ነበር:: ሴኔጋላዊው አማካይ የቡድን አጋሩ የሆነውን ማይክል ኪን በጥፊ ተማቷል::
” ተጫዋቾቼ እንዲጣሉ እፈልጋለሁ:: ስህተት በሚሰራበት ወቅት ምላሽ የሚሰጥ ሰው ያስፈልጋል” በማለት የኤቨርተኑ አሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል:: አሰልጣኙ አክለውም ዳኛው ነገሩን ቀስ ብለው ቢያዩት ይመኙ እንደነበር ሆኖም ግን በህጉ መሰረት ቀይ ካርድ መሆኑን አምነዋል::
ጋና ጌይ በማህበራዊ ሚዲያ ገፁ ላሳየው ባህሪ ይቅርታን ጠይቋል::





