የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ ብሄራዊ ቡድኖች አጭር ምልከታ ( ምድብ ሶስት)

በረከት ፀጋዬ

ምድብ ሶስት

ሞሮኮ፣ ጋና፣ ጋቦን፣ ኮሞሮስ 

ሞሮኮ

  • ተሳትፎ፡  18ኛ ጊዜ
  • ምርጥ ውጤት፡ ሻምፒዮን (1976)
  • አሰልጣኝ፡ ቫሂድ ሃሊልሆድዚች
  • ኮከብ ተጨዋች፡  አሽራፍ ሃኪሚ
ሃኪሚ ከክዋክብት ጋር የሚያሳያውን ብቃት በካሜሩን እንዲደግም ይጠበቃል

ምን ይጠብቃሉ፡ ከ2019 የአፍሪካ ዋንጫ ጥሎ ማለፍ ስንበት መልስ ወደ አሰልጣኝነት ብቅ ያሉት ቦስኒያዊው ሃሊልሆድዚች ብዙ ለውጦችን ፈጥረዋል። ይህም አንጋፋ የነበረውን የቡድን ስብስብ በወጣቶች መቀየር የቻሉበት ይጠቀሳል። በዚ ሂደት ከቼልሲው የክንፍ አጥቂ ሃኪም ዚያች ጋር የፈጠሩት አለመግባባት ተጫዋቹን ወደ አፍሪካ ዋንጫ እንዳይጠራ አድርጎታል።  የዚህን ቁልፍ ተጫዋች በቀላሉ ተከላካዮችን የማለፍ ብቃትና ፍጥነት ማጣታቸው ዋጋ እንዳያስከፍላቸው ያሰጋል።

የአፍሪካን እግር ኳስ በደንብ የሚያውቁት ሃሊልሆድዚች በአህጉሪቱ ትልቅ የውድድር መድረክ ያላቸው አናሳ የውጤት ታሪክ ሌላው በአትላስ አንበሶቹ ላይ ጥያቄ የሚያጭር አጋጣሚ ነው። ምንም እንኳን ለዋንጫው ከሚታጩ ፊት አውራሪዎች ተርታ ባይመደቡም የመስመር ተከላካዩ አሽራፍ ሃኪሚ ወቅታዊ ምርጥ ብቃት ላይ መገኘት ግምቶችን ሊያፋልስ ይችላል። ከፔዤው ኮከብ በተጨማሪ የዎልቭሱ የመሃል ተከላካይ ሮማን ሳይስ፣ የባርሴሎናው አጥቂ አብዴ ኢዛላውዚሊ ለሞሮኮ ተጨማሪ ሃይልን የሚፈጥሩ ከዋክብቶች ናቸው። 

የ2019 አፍሪካ ዋንጫን ጨምሮ በመደበኛ 90 ደቂቃ ጨዋታ አንድም ሽንፈትን ያልቀመሱት ሞሮኮዎች በዚህኛው መድረክ ረጅም ርቀትን መጓዝ ያልማሉ። ምናልባትም ዋንጫውን ለማሸነፍ አቅም እንዳላቸው ጭምር ያስባሉ። ከጠንካራዋ የምድቡ ባላንጣቸው ጋና ጋር የሚያካሂዱት የመክፈቻ ጨዋታ ከወዲሁ የብዙዎችን ቀልብ የሚስብ ሆኖ እናገኘዋለን። ሌሎች የምድቡ ተፎካካሪዎቻቸው አቅም እዚ ግባ የማይባል መሆኑን በመጥቀስ ጋናና ሞሮኮ ከምድቡ ተያይዘው ያልፋሉ በማለት አቋሟሪዎች ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። 

ጋና 

  • ተሳትፎ፡  23ኛ ጊዜ
  • ምርጥ ውጤት፡ ሻምፒዮን (1963፣65፣78፣82) 
  • አሰልጣኝ፡ ሚሎቫን ራጅቫክ
  • ኮከብ ተጨዋች፡ አንድሬ አየው
አየዉ የተቺዎቹን አፍ ለማዘጋት ከዚህ የተሻለ ጊዜ የሚያገኝ አይመስልም።

ምን ይጠብቃሉ፡ ከ1982 ወዲህ ዋንጫውን ከፍ ለማድረግ ባይታደሉም፤ ከጫፍ ደርሰው በሚያስቆጭ መልኩ ይሄን ክብር የተነጠቁበትን ሶስት አጋጣሚዎች መቀየር የጥቋቁር ኮከቦቹ ተቀዲሚ እቅድ ነው። ዳግም ብ/ቡድኑን ለማሰልጠን የተሾሙት ሚሎቫን ራጅቫክ ዋንጫውን የማሸነፍ የቤት ስራ ተሰጥቷቸው ካሜሩን ደርሰዋል። በ2010 አለም ዋንጫ እስከ ሩብ ፍፃሜ የተጓዘውን ቡድን የመሩት እኚሁ ሰርቢያዊ ከዛን ጊዜው ተጫዋቾቻቸው አንድሬ አየው እና ጆናታን ሜንሳህ ብቻ በአሁኑ ስብስብ ውስጥ ይገኛሉ። 

በዛው ዓመት በወጣቶች የተገነባ ቡድን ይዘው ለአፍሪካ ዋንጫ ፍፃሜ ቀርበው የነበረ ቢሆንም በግብፅ 1-0 ተሸንፈው ዋንጫውን አጥተዋል። ራጅቫክ ለወጣቶች ዕድልን በመስጠት አሸናፊ ቡድን መገንባትን ያቅዳሉ።  ለዚህም መቀመጫቸውን አውሮፓ ያደረጉ እንደ ካማልደን ሱሌማና (ሬንስ)፣ ኩዱስ ሞሃመድ (አያክስ)፣ ፊሊክስ አፊና ጂያን (ሮማ) እና ኤድመንድ አዶ (ሸሪፍ) የመሳሰሉ ወጣት ተስፈኞችን በቡድናቸው አካተዋል። ሌላው የ17 አመት ታዳጊ አቡዱል ፋቱ ኢሳሃኩ በጋና ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታው ያሳየው ብቃት አዲሱ አብዲ ፔሌ እስከ መባል ያደረሰው ሲሆን ይሄው ታዳጊ ሌላው የጋና ቁልፍ መሳሪያ በመሆን አፍሪካ ዋንጫውን እንደሚያደምቅ ተስፋ ተጥሎበታል። 

ተጥሎበታል።  ከእነዚህ ታዳጊዎች በተጨማሪ የአርሰናሉ አማካይ ቶማስ ፓርቴ፣ የፓላሱ የፊት አጥቂ ጆርዳን አየው እና የሌይስተሩ የኃላ ደጀን ዳንኤል አማርቴን ልምድ ከወጣቶቹ ጋር በማጣመር ዋንጫውን ማሸነፍ የራጅቫክ ተቀዳሚ እቅድ ይሆናል። ከግብፁ የአፍሪካ ዋንጫ በቱኒዝያ በጥሎ ማለፍ ተሸንፈው የወጡበትን አጋጣሚ ጋናውያን ደግመው መመልከት ፈፅሞ አይፈልጉም ሲል ጋናዊው ስፓርት ጋዜጠኛ ኢብራሂም ሬድዋን አሳንቴ ለቢቢሲ አስተያየቱን ይሰጣል። 

ጋቦን 

  • ተሳትፎ፡  8ኛ ጊዜ
  • ምርጥ ውጤት፡ ሩብ ፍፃሜ (1996፣ 2012)
  • አሰልጣኝ፡ ፓትሪስ ኒቪው
  • ኮከብ ተጨዋች፡ ፔር ኤሜሪክ ኦውባሜያንግ
ኦውባሜያንግ በአርስናል የጠፋውን አቋሙን በጋቦን ማልያ ይፈልጋል

ምን ይጠብቃሉ፡ ጥቁር ግስላዎቹ በምድቡ ጠንካራ ተፎካካሪዎች በመኖራቸው ለማለፍ የሚኖራቸው ተስፋ ጥሩ ሶስተኛ በመሆን ላይ የተንጠለጠለ ሊሆን ይችላል። ለሃገሩ 29 ጎሎችን ያስቆጠረው ፔር ኤሜሪክ ኦውባሜያንግ አሁንም የቡድኑ ኮከብ ተጫዋች ነው። ከመክፈቻው ዋዜማ የተሰማው የኮከቡ አጥቂ በኮቪድ የመያዝ ዜና በቡድኑ የመክፈቻ ጨዋታዎች ላይ ጥላ እንዳያጠላ ያሰጋል።

ያሰጋል። ከኦውባሜያንግ በተጨማሪ ሌላው ወሳኝ የቡድኑ አማካይ ማሪዮ ሌሚና በኮቪድ የተያዘ ተጫዋች ሆኖ ራሱን አግልሏል። አምስተኛ የአፍሪካ ዋንጫውን ለሃገሩ የሚጫወተው ኦባምያንግ ቅዠት የሚመስለውን ወቅታዊ የክለብ አቋሙን በዚህ ውድድር ለመቀየር ተዘጋጅቷል። 

ከዲስፒሊን ግድፈት ጋር በተገናኘ አምበልነቱን የተቀማውና ከሚካኤል አርቴታ ቋሚ 11 ውጪ የተደረገው ኦባ በአርሰናል ቤት የተበላሸውን የእግር ኳስ ህይወቱን በካሜሩን ሊያድስ ይችላል? መልሱን ከውድድሩ ጅማሮ በኃላ ምንመለከተው ይሆናል። ፈረንሳዊው አሰልጣኝ ፓትሪስ ኒቪው ትልቅ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚከብዳቸው ቢጠበቅም የቡድኑን አጠቃላይ ክብር መመለስ እና ጥሩ ውድድር ማሳለፍን ያልማሉ። 

ያለፈውን አፍሪካ ዋንጫ ማለፍ ያልቻሉት ጋቦናውያን የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎችን በትልቅ ተስፋ ቢጀምሩም ተራራውን መሻገር ከብዶዋቸው ከግድግዳዎች ጋር የመላተም ጉዞ ሆኖባቸው አልፏል። እንደ ዲዲዬ ንዶንግ፣ ዬኒ ማትያስፖር የመሳሰሉ ልምድ ያላቸው ተጫዋቾችን የደጋፊውን ድምፅ ሰምተው ያላካተቱት ኒቪው ይህን ያላደረጉት የቡድኑን መንፈስ ለመጠበቅ በማሰብ እንደሆነ ታምኖበታል። ከምድብ ማለፍ ከቻሉ ጥቋቁር ግስላዎቹ ውጤቱን በመልካም ያዩታል። 

ኮሞሮስ

ኮሞሮስ፡ እንደ ቤተሰብ የተገነባው ቡድን
  • ተሳትፎ፡  የመጀመሪያ ጊዜ 
  • ምርጥ ውጤት፡ –
  • አሰልጣኝ፡ አሚር አብዶ
  • ኮከብ ተጨዋች፡  ኤል ፋርዱ ቤን መሃመድ

ምን ይጠብቃሉ፡ የመድረኩ እንግዳዋ ሃገር ኮሞሮስ በቡድኗ ውስጥ ልምድን ያካበቱ ተጨዋቾች መያዟ በቀላሉ እንዳትታይ ያደርጋታል። ወረቀት ላይ ምንም ማድረግ እንደሚቻል ያምናሉ። ኦባምያንግን ከያዘችው ጋቦን ጋር በመክፈቻው ሲገናኙ ሽንፈትን ካስወገዱ ምንም ነገር ሊያደርጉ ይችላሉ። ለትንሿ የባህር ዳርቻ ሃገር ምንም ውጤት ቢመዘገብ ፋይዳው እምብዛም አለመሆኑ በጀብደኝነት እንዲጫወቱ ሊያደርጋቸው ይችላል።

የቡድኑ አምበል ናጂም አብዱ እና ጓደኞቹ ከግብፅ ጋር 0-0 የተለያዩበትን ውጤት ጨምሮ ከጋና፣ ካሜሩን እና ሞሮኮ ጋር ተገናኝተው ማወቃቸው በውድድሩ ላይ የራስ መተማመንን ይጨምርላቸዋል። ከምድብ ማለፍ ከቻሉ እንደ ትልቅ ውጤት ይቆጥሩታል። 

የጨዋታ መርሃ ግብሮች

ሰኞ ጥር 2/2014 

  • ሞሮኮ vs ጋና (ምሽት 1፡00 ሰዓት)
  • ኮሞሮስ vs ጋቦን (ምሽት 4፡00 ሰዓት)

አርብ ጥር 6/2014 

  • ሞሮኮ vs ኮሞሮስ (ምሽት 1፡00 ሰዓት)
  • ጋቦን vs ጋና (ምሽት 4:00 ሰዓት)

ማክሰኞ ጥር 10/2014

  • ጋቦን vs ሞሮኮ (ምሽት 4:00 ሰዓት)
  • ጋና vs ኮሞሮስ (ምሽት 4:00 ሰዓት) 

ምንጮች፡ 

Girmachew Kebede

Related Posts

St. George wins the City Cup 

Ethiopia’s oldest and most successful club St. George have added another trophy to their cabinet by winning the 19th edition of the Addis Ababa City Cup. This is the club’s…

ሐዊ የቺካጎ ማራቶንን አሸነፈች

© Getty Images ኢትዮጵያዊቷ ሐዊ ፈይሳ በባንክ ኦፍ አሜሪካ ቺካጎ ማራቶን ባለድል ሆናለች። መገርቱ አለሙ ደግሞ በሁለተኛነት አጠናቅቃለች። ሐዊ ውድድሩን ያሸነፈችበት ጊዜ 2:14:56 ሲሆን የግሏ ምርጥ ሰዓት ነው።  የዓለም ማራቶን ሜጀር…

Leave a Reply

You Missed

St. George wins the City Cup 

St. George wins the City Cup 

ሐዊ የቺካጎ ማራቶንን አሸነፈች

ሐዊ የቺካጎ ማራቶንን አሸነፈች

Great Ethiopian Run Winners to Receive Record Prize Money

Great Ethiopian Run Winners to Receive Record Prize Money

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለአትሌቶች ከፍተኛውን ሽልማት ሊያበረክት ነው

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለአትሌቶች ከፍተኛውን ሽልማት ሊያበረክት ነው

Ethiopia’s Shure Demise Seeks Third Victory at TCS Toronto Waterfront Marathon

Ethiopia’s Shure Demise Seeks Third Victory at TCS Toronto Waterfront Marathon

የ2025 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ተሸላሚዎች ይፋ ሆኑ

የ2025 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ተሸላሚዎች ይፋ ሆኑ