ይስማው ድሉ እና መልክናት ውዱ የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10 ኪሎ ሜትር አሸነፉ

ይስማው ከሁለቱ አሸናፊዎች የበለጠ አሳማኝ የነበረ ሲሆን ፤ ውድድሩን በ28 ደቂቃ ከ25 ሰከንድ አጠናቋል። ይህም በ2006 ዓ.ም በድሪባ መርጋ ከተመዘገበው የውድድሩ ሪከርድ (28፡16) በ9 ሰከንድ ብቻ ዘግይቶ አጠናቋል። ይህ ድሉ ባለፈው ቅዳሜ በተካሄደው አገር አቋራጭ ማጣሪያ ላይ ለኢትዮጵያ ቡድን ማለፍ ባለመቻሉ የተሰማውን ቁጭት ያስረሳው ሲሆን ፤ በጎዳና እና በትራክ ላይ በሚያደርጋቸው ውድድሮች ግን ባለው ስኬት ላይ ተጨማሪ ድል ሆኖለታል።

ባለፈው ዓመት 3ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ይስማው ፤ በመስከረም ወር መጨረሻ በካርዲፍ ግማሽ ማራቶን በ59 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ በማሸነፍ ጥሩ አቋም ላይ ሆኖ ነበር ወደዚህ ውድድር የመጣው። በበጋው መጨረሻ ላይ ደግሞ በ3፡58.7 በሆነ ሰዓት የመንገድ ማይል በመሮጥ በተለያዩ ርቀቶች ላይ ያለውን አቅም እያሳየ የሚገኝ ወጣት አትሌት ነው። በሁለተኛ ደረጃ አዲሱ ነጋሽ (28:28) እና በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ ድንቃለም አየለ (28:29) በመግባት አጠናቀዋል።

በሴቶች ከሁለት ዓመት በፊት የውድድሩ አሸናፊ የነበረችው መልክናት ውዱ ፤ በመጨረሻዎቹ 150 ሜትሮች ላይ ፍታው ዘርዓይን በማስቀደም ወደ ቀድሞ ፎርሟ መመለሷን አረጋግጣለች። ውዱ ከሁለት ሳምንት በፊት በቦስተን ግማሽ ማራቶን ከሀገሯ ልጅ ፋንታዬ በላይነሽ በመቀጠል 2ኛ ሆና ያጠናቀቀች ሲሆን ፤ ይህም በበጋው ሁለተኛ አጋማሽ በደረሰባት ጉዳት ምክንያት ከውድድር ርቃ ከቆየች በኋላ ነው።

ሁለቱም አሸናፊዎች እያንዳንዳቸው 400,000 የኢትዮጵያ ብር የገንዘብ ሽልማት አግኝተዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ በስፖርት ህይወታቸው በሚቀጥሉበት ጊዜ የአሸናፊነት መለያው ለእነሱ ትልቅ ትርጉም ይኖረዋል። ድሉ ቀጣይ ውድድሩን በታህሳስ 5 በሳውዲ አረቢያ የሚያደርግ ሲሆን፣ ወዱ ደግሞ ለሚቀጥለው የቤት ውስጥ ውድድር (Indoor season) ወደ ትራክ ለመመለስ ትፈልጋለች።ዛሬ መስመሩን ከተሻገሩ የመጀመሪያዎቹ አምባሳደሮች መካከል የኖርዌይ አምባሳደር ሲሆኑ፣ ውድድሩን በ49 ደቂቃ ከ3 ሰከንድ አጠናቀዋል።

ለታላቁ የኢትዮጵያ ሩጫ ተጋባዥ እንግዶች ሆነው የቀረቡት ዳንኤል ኮመን እና ኻሊድ ኻኑቺ ከብዙሃኑ ጋር ኮርሱን ያጠናቀቁ ሲሆን፣ በ44 ደቂቃ እና በ50 ደቂቃ በመግባት ውድድሩን አጠናቀዋል።

🥇 አሸናፊ ወንዶች

  1. ይስማው ድሉ 28:25.2
  2. አዲሱ ነጋሽ 28:28.6
  3. ድንቃለሙ አየለ28:29.2

🥇ሴቶች ሰዓት

  1. መልክናት ውዱ 32:11.2
  2. ፍታው ዘራይ 32:11.5
  3. መሰለች አለማየሁ 32:19.7

Via Great Ethiopian Run

  • Brook Genene

    Brook is a football writer who focuses on sports injuries. He has previously written on local sports for Soccer Ethiopia and Ethiopian Business Review magazine.

    Related Posts

    የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ዳሰሳ

    በበረከት ጸጋዬ 35ተኛው የአፍሪካ ዋንጫ (ከታህሳስ 21 እስከ ጥር 10/2018) በሞሮኮ የሚካሄድ ሲሆን የወቅቱ ሻምፒዮን አይቮሪኮስት :ደቡብ አፍሪካ እና መሰል ሀገራት ከሚቀጥለው አመት የፊፋ የአለም ዋንጫ ቀደም ብለው በአህጉራዊ ውድድሩ…

    ሞ ሳላህ ላይ እየተሰጡ ያሉ ትችቶች እንዴት ይታያሉ? 

    ግብጻዊው የሊቨርፑል የፊት መስመር ተጫዋች ሞ ሳላህ ከሊዲሱ ጨዋታ መልስ በሰጠው አስተያየት መነጋገሪያ ሆኖ ከርሟል፡፡  “ 90 ደቂቃ ሙሉ ተጠባባቂ ወንበር ላይ መሆኔን ላምን አልችልም፡፡ ለሶስተኛ ተከታታይ ጨዋታ ነው ይህ…

    You Missed

    የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ዳሰሳ

    የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ዳሰሳ

    ሞ ሳላህ ላይ እየተሰጡ ያሉ ትችቶች እንዴት ይታያሉ? 

    ሞ ሳላህ ላይ እየተሰጡ ያሉ ትችቶች እንዴት ይታያሉ? 

    ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች

    ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች

    Qatar to build 11 running tracks in 11 countries

    Qatar to build 11 running tracks in 11 countries

    በአፍሪካ ትምህርት ቤቶች የእግር ኳስ ሻምፕዮና የሴካፋ ማጣሪያ ኢትዮጵያ በሁለቱም ጾታ ለፍጻሜ አለፈች

    በአፍሪካ ትምህርት ቤቶች የእግር ኳስ ሻምፕዮና የሴካፋ ማጣሪያ ኢትዮጵያ በሁለቱም ጾታ ለፍጻሜ አለፈች

    ቀይ ቀበሮዎቹ ካታር ለመገኘት በሞሮኮ ይፋለማሉ

    ቀይ ቀበሮዎቹ ካታር ለመገኘት በሞሮኮ ይፋለማሉ