
ባለፈው አመት በፓሪስ በተካሄደው የኦሎምፒክ ውድድር አልጄሪያዊቷ አትሌት ኢማን ካሊፍ ከፆታ ተገቢነት አንፃር በርካታ ጥያቄዎች ሲነሱባት እንደነበር የሚታወስ ነው::
ከዚህ በመቀጠልም በሌሎች ውድድሮች ለመሳተፍ ግዴታ ምርመራ ማድረግ እንዳለባት የሚገልፁ ደንቦች ወጥተዋል::
የአለም አትሌቲክስ ማህበር በቅርቡ ባወጣው መግለጫ መሰረትም አትሌቶች ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚደረግ የፆታ ምርመራ ማከናወን ይጠበቅባቸዋል::
ይህ ምርመራ የወንዱ Y ክሮሞዞም ላይ የሚገኘውን SRY ዘረ መል ወይንም በተለምዶ ‘ፆታ የሚለይ ዘረ መል ‘ የተባለውን መርምሮ ማወቅ የሚያስችል ነው::ምርመራው ከጉንጭ የውስጠኛው ክፍል በሚወሰድ ናሙና ወይንም በደም ምርመራ የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የአለም አትሌቲክስ ፕሬዝዳንት ሰባስቲያን ኮ “ የሴቶችን ስፖርት በጥንቃቄ መያዝ እና ትክክለኛነቱን መጠበቅ ያስፈልጋል” በማለት ተናግረዋል:: “በርካታ ሴቶች እንዲወዳደሩ ስለምንፈልግ ትክክለኛ አሰራሮችን መከተል አለብን” በማለትም ገልፀዋል::
“ የY ክሮሞዞምን ብቻ መመልከት በራሱ አንድ ሰው ሴት ወይንም ወንድ ለመሆኑ በቂ ማረጋገጫ ነው ማለት አይደለም” በማለት በማንችስተር ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ የስፖርት ፕሮፌሰር የሆኑት አሉን ዊልያምስ ለቢቢሲ በሰጡት መግለጫ ይናገራሉ::
እንደባለሙያው ገለፃ ጥሩ ጠቋሚ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ግን አጥጋባቢ መልስ የሚሰጥ ነው ማለት አይቻልም::
ከፆታ አፈጣጠር ጋር ተያይዞ ህመም ያለባቸው ሰዎች ያላቸው Y ክሮሞዞም በበቂ ሁኔታ የዳበረ አይደለም:: የተወሰኑ የተሰወሩ የዘረ መል አካላት ሊኖሩ ይችላሉ::
SRY ዘረ መልን ማወቅ ግን ከY ክሮሞዞም በተሻለ ጥሩ ምልክቶችን ይሰጣል::
ተጨማሪ የቴስቴስትሮን ንጥረ ነገር መያዝ ከሚሰጣቸው ጥቅሞች መካከል ተለቅ ያለ የጡንቻ ግዝፈት : የጠነከሩ እና የረዘሙ አጥንቶች እንደዚሁም እንደሳንባ እና ልብ ያሉ የሰውነት አካላት መጨመርም ይካታቱበታል:: እነዚህ የተለዩ ጥቅሞች ያላቸው አትሌቶች በሴቶች ስፖርት በመግባት ውድድሩን የአንድ ወገን ብቻ እንዳያደርጉት እየሰራሁ ነው በማለት የአለም አትሌቲክስ ገልፆል::