
በዛሬው ጨዋታ አርሰናል ከታክቲካዊ ነገሮች በላይ ሁለት መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት የሚያስፈልገው ይመስለኛል።̏
- አዕምሮ
ካርሎ አንቼሎቲ ደጋግመው እንደሚናገሩት የዛሬው አይነት ጨዋታዎች ከታክቲክ ይልቅ የስሜት ፍልሚያዎች ናቸው። ሚኬል አርቴታም ከጨዋታው በፊት ስለ ስሜት አብዝቶ የተናገረው ለእዚህ ይመስላል። ለአርሰናል የተረጋጋ ስሜት፣ ጎል ቀድሞ ቢቆጠርበት እንኳን የማይሰበር መንፈስ እጅግ ያስፈልገዋል። - ለዳኛ እድል አለመስጠት
ቀጣዩን የምፅፈው ዳኞች ለማድሪድ ያደላሉ ለማለት አይደለም። ሆኖም ትልልቆቹ ቡድኖች በሜዳቸው በሚያደርጓቸው ጨዋታዎች የ50፣ 50 የዳኛ ውሳኔዎች ተጠቃሚዎች ይሆናሉ። ቲዬሪ ኦንሪ ለሲቢኤስ አርሰናል በሀይበሪ እና ዩናይትድ በኦልድ ትራፎርድ የእንደዚህ አይነት ውሳኔዎች ተጠቃሚ እንደነበሩ ተናግሯል። ይህ ባለፉት ዓመታት የቻምፒየንስ ሊግ ፍልሚያዎች በቤርናቢዩ የተመለከትነው ነው። በዛሬው ጨዋታም ትልቁ የአርሰናል ጥንቃቄ የሚሆነው ዳኛው በተለይ ካርድ እንዲመዝ በተቻለ መጠን እድል አለመስጠት ይሆናል።