የጀርመን ብሄራዊ ቡድን የ2014ቱን የአለም ዋንጫ ካሸነፉ ማግስት አንድ ከባድ ነገርን መጋፈጥ ነበረባቸው:: ኑሮ ያለድንቁ አጥቂ ሚሮስላቭ ክሎዘ! በአሁኑ ሰአት በጀርመን ሁለተኛ ዲቪዚዮን የቡንደስሊጋ ዋንጫን ብዙ ጊዜ በማሸነፍ ሁለተኛ ላይ ያሉትን ኑረንበርግ የሚያሰለጥነው ክሎዘ በርካታ ግቦችን በአለም ዋንጫ የማስቆጠር ሬከርድን ከሮናልዶ ፊኖሜኖ ከወሰደ ማግስት የብሄራዊ ቡድን አገልግሎት በቃኝ ብሏል:: ይህ transition ለዳይ ማንሻፍት ቀላል አልነበረም:: ዩሮ 2016 ላይ በግማሽ ፍፃሜው በፈረንሳይ ሲሰናበቱ የፊት መስመሩን ይመራው የነበረው ማሪዮ ጎሜዝ ነበር:: ከዛ ውድድር በኃላ ግን በተለይም ጀርመን ውጤት ባጣችባቸው ውድድሮች ሁነኛ የ9 ቁጥር ተጫዋች ለረጅም ጊዜ አልነበረም:: እንደቲሞ ቨርነር አይነት ተጫዋቾች ቦታው ትልቅ ሆኖባቸው ታይቷል:: አሁን ግን በጁሊያን ናግልስማን የሚመራው ቡድን ወሳኝ አጥቂ ያገኘ ይመስላል:: የኒውካስሉ አጥቂ ኒክ ዋልተማደ ዘንድሮ ድንቅ አቋም ላይ ይገኛል:: ፕሪሚየር ሊጉን ለመላመድም ጊዜ አልፈጀበትም:: ከኃላው የሙሲዬላ እና ቨርትዝን እርዳታ የሚያገኘው ዋልተማደ ለሀገሩ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል::
በስተመጨረሻም ጀርመን የምትፈልገውን አጥቂ ሳታገኝ አትቀርም!




