የ2025 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ተሸላሚዎች ይፋ ሆኑ

የ2025 አፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ የዘንድሮ የክብር ተሸላሚዎች ታውቀዋል። ይህ አመታዊ የእውቅና ሽልማት ስነ ስርአት በሙያቸው ታላቅ ሥራ የሰሩ ግለሰቦችን ለማክበር የሚሰናዳ ነው። በየአመቱ ከስፖርት፣ ከስነ ጥበብና ከቢዝነስ ዘርፎች ለማህበረሰቦቻቸው ላበረከቱት አስተዋፅኦና ለለውጥ ላደረጉት የላቀ ተሳትፎ ከየዘርፉ ተመርጠው የሚሸለሙበት መድረክ ነው።

አፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ እስካሁን ለ5 ጊዜያት ተካሂዷል። እውቅና ከተሰጣቸው ተፅዕኖ ፈጣሪዎች መካከል ደግሞ የሚከተሉት ይገኙበታል፦

2019: ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን( ቴዲ አፍሮ)፣ አትሌት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉና ሚስተር ማርክ ጌልፋንድ

2020: በኮቪድ-19 ምክንያት አልተካሄደም

2021: አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ፣ ድምፃዊ ኤኮንና አቶ በረከት ወልዱ

2022: አትሌት ቀነኒሳ በቀለ፣ “እረኛዬ” የቴሌቪዥን ድራማ፣ አቶ ሄኖክ ተስፋዬ እና ንግስት ሰናይ ልኬ

2023: የዲባባ ቤተሰብ፣ አቶ ግርማ ዋቄ፣ አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄና አትሌት ስለሺ ስህን

2024: ድምፃዊት አስቴር አወቀ፣ ጋዜጠኛ መአዛ ብሩ፣ አትሌት ትዕግስት አሰፋና ጉዳፍ ፀጋዬ፣ እና ርብቃ ሀይሌ ።

ዘንድሮም በተለያዩ ዘርፎች አምስት ተፅዕኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያዊያንን ለማክበርና እውቅና ለመስጠት ዝግጅቱ ተጠናቋል፤ በስፖርቱ ዘርፍ የኦሎምፒክ እና የአለም ሻምፕዮን ሜዳሊያዎች ባለቤት አትሌት መሰረት ደፋር፣ በቢዝነስ ዘርፍ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ ባለሃብቱ ጆ ማሞ፣ በስነ ጥበብ ዘርፍ አንጋፋው ድምፃዊ መሃሙድ አህመድ፣ እና ታዋቂው የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያ ሰይፉ ፋንታሁን ተሸላሚዎች ይሆናሉ።

ዝግጅቱ በጊፍት ሪል ስቴት የአቅራቢ ስፖንሰርነት የሚታገዝ ሲሆን፤ በእለቱ የዲሲ፣ ሜሪላንድና ቨርጂኒያ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ሴናተሮች፣ ከንቲባዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረጋላቸው በርካታ እንግዶች ይገኛሉ፤ ተሸላሚዎቹ ከግዛቶቹና ከተማዎቹ ተወካዮች የእውቅና ሰርተፍኬት ይበረከትላቸዋል። በተጨማሪ የሙዚቃ ዝግጅት የሚቀርብ ይሆናል። ዝግጅቱ በሜሪላንድ ስቴት ሲልቨር ስፕሪንግ በሚገኘው ሲቪክ ህንፃ ኦክቶበር 12 ምሽት በርካታ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ተጋባዥ እንግዶች እና በርካታ የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች በሚገኙበት ይከናወናል።

(ግራንድ አፍሪካን ረን)

Girmachew Kebede

Related Posts

St. George wins the City Cup 

Ethiopia’s oldest and most successful club St. George have added another trophy to their cabinet by winning the 19th edition of the Addis Ababa City Cup. This is the club’s…

ሐዊ የቺካጎ ማራቶንን አሸነፈች

© Getty Images ኢትዮጵያዊቷ ሐዊ ፈይሳ በባንክ ኦፍ አሜሪካ ቺካጎ ማራቶን ባለድል ሆናለች። መገርቱ አለሙ ደግሞ በሁለተኛነት አጠናቅቃለች። ሐዊ ውድድሩን ያሸነፈችበት ጊዜ 2:14:56 ሲሆን የግሏ ምርጥ ሰዓት ነው።  የዓለም ማራቶን ሜጀር…

You Missed

St. George wins the City Cup 

St. George wins the City Cup 

ሐዊ የቺካጎ ማራቶንን አሸነፈች

ሐዊ የቺካጎ ማራቶንን አሸነፈች

Great Ethiopian Run Winners to Receive Record Prize Money

Great Ethiopian Run Winners to Receive Record Prize Money

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለአትሌቶች ከፍተኛውን ሽልማት ሊያበረክት ነው

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለአትሌቶች ከፍተኛውን ሽልማት ሊያበረክት ነው

Ethiopia’s Shure Demise Seeks Third Victory at TCS Toronto Waterfront Marathon

Ethiopia’s Shure Demise Seeks Third Victory at TCS Toronto Waterfront Marathon

የ2025 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ተሸላሚዎች ይፋ ሆኑ

የ2025 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ተሸላሚዎች ይፋ ሆኑ