ትዝብት፡ አርሰናል ለምን ብዙ ጎሎች አይቆጠሩበትም?

አርሰናል ከትልልቆቹ ቡድኖች የሚለይበት አንድ ነገር ያለ ይመስለኛል። አብዛኛዎቹ ቡድኖች በጥልቀት በሚከላከሉበት ወቅት ቢያንስ የአንድ ወይም የሁለት ተጫዋቾችን የመከላከል ጫናን ያቀሉላቸዋል። በጥልቀት በሚከላከሉበት ጊዜ 9+1 ወይም 8+2 ሊባል ይችላል። ይህ ከጫና ማምለጫ መንገድ ይሰጣቸዋል። በተለይ የጎል አስቆጣሪዎቻቸውን በመከላከል ብዛት የሚመጣ ድካም በመቀነስ በተቃራኒው ሳጥን ኳስ በሚያገኙበት ጊዜ ፍሬሽ እንዲሆኑ ያግዛል።

የዘንድሮው ሞ ሳላን ልብ ይሏል። የመከላከል ጫናው ቀንሶለት ወደ ራሱ የግብ ክልል ብዙ ሩጫዎችን ሲያደርግ አይታይም። ይህ ሙሉ ለሙሉ አይከላከልም ማለት ግን አይደለም።

በአርሰናል ቤት ግን ትንሽ የተለየ ነው። ቡድኑ የተጋጣሚ የግብ ክልል ላይ ኳስ ተነጥቆ ወዲያው መልሶ ለመንጠቅ ካልቻለ እንደ ቡካዮ ሳካ አይነት ተጫዋቾች ሳይቀር ከ40-50 ሜትር በፍጠነት ወደ ግብ ክልላቸው እንዲመለሱ ያደርጋል። ማርቲኔሊም አይቀርለትም። ሜሪኖም እስከ ቡድኑ ፍ.ቅ.ም ክልል ድረስ መመለሱ አይቀርም።

ሁሉም ተጫዋቾች ከኳስ ጀርባ ይሆናሉ። ጥብቅ የመከላከል ቀጠናም ይዘረጋሉ። ምናልባት አርሰናል የማይሽነፈው በዚህ ምክንያት ይሆናል።

ከዚህ በታች በታያዩዙት የመጀመሪያ ሁለት ምስሎች እንደምትመለከቱት ኩርቷ ኳሱን በሚለቅበት ሰከንድ እና አርሰናል በጥልቀት የመከላከል ቅርፅ መካከል ያለው ልዩነት 20 ሰከንድ ብቻ ነው፡፡

ሁሉም የአርሰናል ተጫዋቾች ወደ ግብ ክልላቸው ተመልሰው ኳስ ጀርባ ለመሆን የወሰደባቸው ጥቂት ሰከንዶች ነው።

የአርሰናል ተጫዋቾች በሙሉ ወደ መከላከል ዞን ተመልሰዋል

አርሰናል ኳሱን ቢነጥቁ እንኳን ለመልሶ ማጥቃት የሚሆን ቦታ ላይ የሚገኝ ተጫዋች የለም

ምስል ፟ ከሪያል ማድሪድ የማጥቃት እንቅስቃሴ ያለ ክፍት ቦታ

ማድሪድ ኳሱን ወደ ቀኝ መስመር ሲወስደው ደግሞ ሁሉም ተጫዋቾች ያለምንም outlet ሲከላከሉ ትመለከታላችሁ። ኳሱን ለመንጠቅም ችለዋል።

  • Girmachew Kebede

    Related Posts

    አዲሱ የአሎንሶ አብዮት; የጨዋታ ቁጥጥር እና ከኳስ ውጪ የተጨዋቾች ሚና

    ከላይ የተጠቀሱት ሃሳቦች አውሮፓ ውስጥ ላሉ ታላላቅ ክለቦች እና አሰልጣኞቻቸው አዲስ ነገር አይደሉም:: በእግርኳስ ከፍ ባለው ልህቀት ደረጃ ላይ የደረሱ አሰልጣኞች ዋነኛ አላማቸው የጨዋታውን አካሄድ መቆጣጠር ነው:: ይህም ተጋጣሚን አጨዋወቱን…

    በሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ዙሪያ የስፖርት ግልግል ፍርድ ቤት ምን ይላል?

    ከአራት ሳምንታት በፊት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብን “የታገዱ ተጫዋቾችን በማሰለፍ” በሚል በኢትዮጵያ ዋንጫ ያገኘው ድል ተሰርዞ በፎርፌ እንዲሽነፍ እና የቀጣዩ የውድድር ዘመን የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ…

    You Missed

    St. George wins the City Cup 

    St. George wins the City Cup 

    ሐዊ የቺካጎ ማራቶንን አሸነፈች

    ሐዊ የቺካጎ ማራቶንን አሸነፈች

    Great Ethiopian Run Winners to Receive Record Prize Money

    Great Ethiopian Run Winners to Receive Record Prize Money

    ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለአትሌቶች ከፍተኛውን ሽልማት ሊያበረክት ነው

    ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለአትሌቶች ከፍተኛውን ሽልማት ሊያበረክት ነው

    Ethiopia’s Shure Demise Seeks Third Victory at TCS Toronto Waterfront Marathon

    Ethiopia’s Shure Demise Seeks Third Victory at TCS Toronto Waterfront Marathon

    የ2025 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ተሸላሚዎች ይፋ ሆኑ

    የ2025 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ተሸላሚዎች ይፋ ሆኑ