
Channels and closing them (በተለምዶ->መዝጋት)
Channel በብሪቲሾቹ እንግሊዝኛ ቦይ የሚለውን ፍቺ ይይዛል:: ውሃ ያለገደብ የሚወርድበት መንገድ እንደማለት ነው:: በእግርኳሱም ይህንኑ ሃሳብ በመዋስ የሜዳ ላይ ቦዮችን ማግኘት ይቻላል:: የተጋጣሚ ተጨዋቾችን አደራደር መነሻ በማድረግ በመሃከላቸው ያለውን ክፍተት channel ብለን እንጠራዋለን::
በሜዳው ዳር እና መስመር ተጨዋቾችም(wingers and fullbacks) እንደዚሁ channel አለ:: ምስሉ እንደሚያሳየው 5 ቻናሎች አሉ:: የግራ እና ቀኝ : ውስጣዊ ግራ እና ቀኝ እንዲሁም የመኅል ቻናል ይባላሉ:: ውስጣዊ ግራ እና ቀኝ ቻናሎች ዘመናዊው እግርኳስ ስማቸውን ወደ “ሀፍ ስፔስ” half space ቀይሮታል::
ከዚህ በተጨማሪም ከ 4-3-3 በእግርኳሱ ተመራጭነት መጨመር እና መግነን በኅላ የመኅል channel ሞቷል የሚሉም አሉ:: ይህም የሆነበት ምክንያት የ 4-3-3 single pivot ከኳስ ውጪ ዋነኛ አላማ ይህንን መስመር መዝጋት ስለሆነ ነው::
በዚሁ አሁን ስለተጠቀምኩት ‘መስመር መዝጋት’ ስለሚለው ጉዳይ ; መስመር መዝጋት ወይም closing the channel/ channels በቀጥታ ኳስ የያዘው ተጨዋች ላይ የሚደረግ ተግባር ሳይሆን ከእንቅስቃሴው ሩቅ ያሉ ተቀባዮች በምቾት ኳስ እንዳይቀበሉ ከኳስ ውጪ ያሉት ተጨዋቾች የሚቆሙበት የተጠና አቋቋም ነው::
ለምሳሌ እሁድ እለት በተካሄደው የማንቸስተር ሲቲ እና ሊቨርፑል ጨዋታ ባለሜዳዎቹ ፊል ፎደንን በ ቀኝ ቻናላቸው በተደጋጋሚ ለማግኘት ይሞክሩ ነበር:: ፎደንን በዛ ቦታ አግኝቶ ሳቪንዮን በመስመር ሰንጣቂ ኳስ ወደአደጋ ቀጠና ለማስገባት የታለመ እቅድ ነበር:: ዶመኒክ ሶቦዝላይ ግን ይህንን ቻናል የመዝጋት ኅላፊነት ተሰጥቶት ነበር:: ምንም እንኳን ሃንጌርያዊው ከፊት ፕሬሲንጉን የማስጀመር ኅላፊነት ቢኖርበትም በተደጋጋሚ ከጀርባው እየቃኘ አቋቋሙን ያስተካክል ነበር:: ይህም ፎደን ኳስ መቀበል እንዳይችል አድርጎታል::
ስለዚህ ጎሎች ሲቆጠሩ በተለይ ከአሲስቱ በፊት የተደረጉ ፓሶች ለምን እና እንዴት ተደረጉ? እነዚህ ፖሶች እዳይደረጉ ምን መደረግ ነበረበት? የሚሉት ነገሮች እግርኳስን ስንመለከት መታዘብ እንዳንረሳ::

Pic- the different types of channels on a football pitch… image via Google
Minyahel Mamo is a certified video and tactical analyst in Addis Ababa.