
የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ የሆኑት ኢትዮጵያ መድን በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ የዛንዚባሩን ክለብ ምላንዴግ ይገጥማሉ:: የመጀመሪያ ጨዋታቸውንም በሜዳቸው ያደርጋሉ።
ኢትዮጵያ መድን አሸናፊ ከሆኑ በሁለተኛው ዙር ከፒራሚድስ እና “APR” አሸናፊ ጋር ይጫወታሉ።
የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ከ መስከረም 9-11/2018 እንዲሁም የመልስ ጨዋታው ከ መስከረም 16-18/2018 ሊደረግ እንደታቀደ ይታወቃል።

ወላይታ ድቻ በበኩላቸው ከአንድ የሊቢያ ክለብ ጋር እንደሚጫወቱ ታውቋል የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታም በሜዳቸው ያደርጋሉ::
ሊቢያን የሚወክለው ቡድን ያልታወቀ ሲሆን በቀጣይ ሀገሪቷ ይፋ እንደምታደርግ ይጠበቃል።
የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ከ መስከረም 9-11/2018 እንዲሁም የመልስ ጨዋታው ከ መስከረም 16-18/2018 የሚካሄድ ሲሆን ወላይታ ድቻ በደርሶ መልስ የሚያሸንፉ ከሆነ ከግብጹ አል መስሪ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።
