ሪያል ማድሪድ ከአርሰናል: ቅድመ ጨዋታ ነጥቦች

በዛሬው ጨዋታ አርሰናል ከታክቲካዊ ነገሮች በላይ ሁለት መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት የሚያስፈልገው ይመስለኛል።̏

  1. አዕምሮ
    ካርሎ አንቼሎቲ ደጋግመው እንደሚናገሩት የዛሬው አይነት ጨዋታዎች ከታክቲክ ይልቅ የስሜት ፍልሚያዎች ናቸው። ሚኬል አርቴታም ከጨዋታው በፊት ስለ ስሜት አብዝቶ የተናገረው ለእዚህ ይመስላል። ለአርሰናል የተረጋጋ ስሜት፣ ጎል ቀድሞ ቢቆጠርበት እንኳን የማይሰበር መንፈስ እጅግ ያስፈልገዋል።
  2. ለዳኛ እድል አለመስጠት

ቀጣዩን የምፅፈው ዳኞች ለማድሪድ ያደላሉ ለማለት አይደለም። ሆኖም ትልልቆቹ ቡድኖች በሜዳቸው በሚያደርጓቸው ጨዋታዎች የ50፣ 50 የዳኛ ውሳኔዎች ተጠቃሚዎች ይሆናሉ። ቲዬሪ ኦንሪ ለሲቢኤስ አርሰናል በሀይበሪ እና ዩናይትድ በኦልድ ትራፎርድ የእንደዚህ አይነት ውሳኔዎች ተጠቃሚ እንደነበሩ ተናግሯል። ይህ ባለፉት ዓመታት የቻምፒየንስ ሊግ ፍልሚያዎች በቤርናቢዩ የተመለከትነው ነው። በዛሬው ጨዋታም ትልቁ የአርሰናል ጥንቃቄ የሚሆነው ዳኛው በተለይ ካርድ እንዲመዝ በተቻለ መጠን እድል አለመስጠት ይሆናል።

Girmachew Kebede

Related Posts

አቋማቸው የዋዠቀ አምስት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች

ሁለቱ የማንችስተር ክለቦችን ጨምሮ 5 ቡድኖች ባለፉት ሶስት አመታት የዋዥቀ አቋምን እንዳሳዩ CryptoCasinos  ያወጣው ቁጥራዊ መረጃ ያሳያል:: የ20 ጊዜ የፕሪሚየር ሊግ አሸናፊዎቹ ከትልቁ ዋንጫ ከራቁ 12 አመታት ተቆጥረዋል:: ከ2022/23 አንፃር…

በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረው የአጥቂዎች ዝውውር 

ከጥቂት አመታት በፊት ይህ ነው የሚባል የዘጠኝ ቁጥር ተጫዋች አልነበረም፡፡ ይህም በርካታ ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦችን ያሳስብ ነበር፡፡ በተለይም በ2010ቹ ገነው ከወጡት እንደሉዊስ ስዋሬዝ ፤ ሰርጂዮ አግዌሮ ፤ ካሪም ቤንዚማ ፤…

Leave a Reply

You Missed

St. George wins the City Cup 

St. George wins the City Cup 

ሐዊ የቺካጎ ማራቶንን አሸነፈች

ሐዊ የቺካጎ ማራቶንን አሸነፈች

Great Ethiopian Run Winners to Receive Record Prize Money

Great Ethiopian Run Winners to Receive Record Prize Money

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለአትሌቶች ከፍተኛውን ሽልማት ሊያበረክት ነው

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለአትሌቶች ከፍተኛውን ሽልማት ሊያበረክት ነው

Ethiopia’s Shure Demise Seeks Third Victory at TCS Toronto Waterfront Marathon

Ethiopia’s Shure Demise Seeks Third Victory at TCS Toronto Waterfront Marathon

የ2025 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ተሸላሚዎች ይፋ ሆኑ

የ2025 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ተሸላሚዎች ይፋ ሆኑ