የቀድሞው የቼልሲ የመሀል ተከላካይ ጆን ቴሪ ጥር ላይ በተሰናበቱት አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ምትክ የጊዜያዊ አሰልጣኝነት እድል ባለማግኘቱ ደስተኛ እንዳልሆነ ገልጿል፡፡
ጆን ቴሪ በቼልሲ አካዳሚ በበጎ ፈቃድ አሰልጣኝነት በወር ሁለት ቀን የሚሰራ ሲሆን ከማሬስካ መሰናበት በኋላ በማንችስተር ሲቲ እና በፉልሃም ጨዋታ የአሰልጣኝነት ቡድን አባል አለመሆኑ እንዳስከፋው ገልጿል፡፡
የ21 አመት በታች ቡድን አሰልጣኝ የሆነው ካለም መክፋርለን ጊዜያዊ አሰልጣኝ በመባል ተሹሞ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡
ጆን ቴሪ በሰጠው አስተያየት በቡድኑ ውስጥ ዋና አሰልጣኝ ባይሆን እንኳን አለመካተቱ ቅር እንዳሰኘው ተናግሯል፡፡




