ኢትዮጵያ ከሴራሊዮን- ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ
አትዮጵያ በገብረመድህን ኃይሌ ስር የምታደርገው የመጀመሪያው ጨዋታ ይሆናል:: ለ2026 አለም ዋንጫ በሚደረገው ማጣሪያ ኢትዮጵያ ሴራሊዮንን ምሽት 4 ሰዓት ላይ በኤል-አብዲ ስቴዲየምትገጥማለች:: ኢትዮጵያ የአለም ዋንጫ ማጣሪያዋን ሴራሊዮንን በመግጠም ትጀምራለች:: የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በአዲሱ አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሃይሌ እየተመራ የመጀመሪያውን የነጥብ ጨዋታያደርጋል:: ከጅማ አባ ጅፋር እና መቀለ 70 አንደርታ ጋር የፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ መሆን የቻሉት እና ኢትዮጵያ መድንከመጡም በኃላ የተሳካ ቆይታን ያደረጉት አሰልጣኝ ገብረመድን ከውጤት ከራቀ ሰንበትበት ያለውን ብሄራዊቡድን የማንሰራራት ከፍተኛ ኃላፊነት አለባቸው:: የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ደካማ እንቅስቃሴ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን ከምድቡምበ4 ነጥብ መጨረሻ በመሆን ነበር ያጠናቀቀው:: ብሄራዊ ቡድኑ በሰኔ 2022 ግብፅ ላይ ካስመዘገበው ድንቅ ብቃት መልስ በቻን ውድድርም ሆነ በማጣሪያጨዋታዎች ደካማ እንቅስቃሴን አሳይቷል:: ይህም ለአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከኮንትራታቸው መጠናቀቅ ቀደምብሎ ከስራ ለመልቀቅ ምክንያት ሆኗል:: የውበቱ ቡድን ኳስን አዘውትሮ የመቆጣጠር ልምድ ቢኖረውም አደገኛ ክልል ውስጥ ከመገኘት እና እድሎችንከመፍጠር አንፃር ብዙ ጥያቄዎች የሚነሱበት ነበር:: ገብረመድህን በቅድመ ጨዋታ መግለጫቸው ” በራሳችንሜዳ ብዙ የመቆየት ነገር አይኖርም ” በማለት መናገራቸው የተለየ ነገርን ይዘው ለመምጣት እንዳሰቡ ፍንጭንየሰጠ ነበር:: “ከኳስ ውጭ ያለን እንቅስቃሴ በጣም ደካማ ነው ፤ ይሄንንም ለማሻሻል በጣም እየሰራን ነው። ሁሌም ቢሆንኳስ ስናጣ ሁላችንም መሮጥ ይኖርብናል:: ከዚህ አንፃር መጠነኛ ለውጦች ቢኖርም ይበልጥ በጊዜ ሂደት ግፊትአሳድረን የምንሰራበት ከሆነ ሊመጣ ይችላል” በማለትም ምን ላይ አተኩረው ልምምዳቸውን እንደተገበሩገልፀዋል:: ዋልያዎቹ የወሳኝ አጥቂዎቻቸውን ግልጋሎት አያገኙም:: ሽመልስ በቀለ እንደዚሁም ለረጅም ጊዜ ጉዳት ላይየከረመው አቡበከር ናስር አይጫወቱም:: ከዚህ ቀደም እራሱን ከብሄራዊ ቡድን ያገለለው ጌታነህ ከበደበውሳኔው መፅናቱን ለማወቅ ተችሏል:: የባህር ዳሩ አማካይ አለልኝ አዘነ ከቡድኑ ጋር አለመኖር በብዙዎች ዘንድ ጥያቄን ያስነሳ ነበር:: በእርሱ ቦታ ላይያሉት ጋቶች ፓኖም እና ናትናኤል ዘለቀ የተሻለ ብቃት ላይ በመኖራቸው መመረጣቸውን ገብረመድህንተናግረዋል:: ተጋጣሚው ቡድን ሴራሊዮን እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ አልቻሉም:: ለዚህ ጨዋታ ባደረጉትዝግጅት ከቤኒን ጋር አቻ ሲወጡ ሱማሊያን አሸንፈዋል:: ሴራሊዮን በአዲሱ አሰልጣኝ አሚዱ ካሪም እየተመራች ትቀርባለች:: ካሪም ከኢትዮጵያ ከባድ ፉክክርእንደሚጠብቁ እና ተጋጣሚያቸው በቀላሉ እጅ እንደማትሰጥ ተናግረዋል::
ኤልክላሲኮ; የሬያል ማድሪድ ውሳኔዎች እና ያስከተሉት ውጤት
የስፔን የክለብ እግርኳስ ታላቁ ፍልሚያ ተደርጓል። በሊጉ የዋንጫ ፉክክር አሸናፊውን ይጠቁማል ተብሎ የተጠበቀው ጨዋታ በ ባርሴሎና የበላይነት ተደምድሟል። ብዙ ክስተቶችን ባስተናገደው ይህ ጨዋታ የ ሬያል ማድሪድን ታክቲካዊ አቀራረብ እና በጨዋታ…
ሌስተር ሲቲ ከ አርሴናል: የትሮሳርድ ልዩ ሚና እና የሌስተር ሲቲ ምላሽ
አርሴናል ወደ ኪንግ ፓወር ስቴድየም ተጉዞ ሌስተር ሲቲን በማሸነፍ በዋንጫው ፉክክር መሪነቱን ያስቀጠለበት ሦስት ነጥብ ማግኘት ችሏል። ሁለተኛው አጋማሽ ጅማሬ ላይ በማርቲኔሊ ብቸኛ ጎል ጨዋታውን ማሸነፍ የቻሉት መድፈኞቹ በጨዋታው ከወትሮው…
አሌክሳንደር ኢሳክ፡ ትውልደ ኤርትራዊው አዲስ የኒውካስል አጥቂ
Alexander Isak – Newcastle United- Getty Images
የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ ብሄራዊ ቡድኖች አጭር ምልከታ ( ምድብ ስድስት)
በረከት ፀጋዬ ምድብ ስድስት ቱኒዝያ፣ ማሊ፣ ሞሪታንያ፣ ጋምቢያ ቱኒዝያ ● ተሳትፎ፡ 20ኛ ጊዜ ● ምርጥ ውጤት፡ ሻምፒዮን (2004) ● አሰልጣኝ፡ ሞንድሄር ኬባይር ● ኮከብ ተጨዋች፡ ሃኒባል መጅብሪ ምን ይጠብቃሉ፡ የአለም…
የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ ብሄራዊ ቡድኖች አጭር ምልከታ ( ምድብ አምስት)
በረከት ፀጋዬ ምድብ አምስት አልጄሪያ፣ ሴራሊዮን፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ አይቮሪኮስት አልጄሪያ ተሳትፎ: 19ኛ ጊዜ ምርጥ ውጤት፡ ሻምፒዮን (1990፣2019) አሰልጣኝ፡ ጀማል ቤልማዲ ኮከብ ተጫዋች፡ ሪያድ ማህሬዝ ምን ይጠብቃሉ፡ አልጄሪያ የአፍሪካ ዋንጫ ክብራቸውን ለማስጠበቅ ብቻ…
የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ ብሔራዊ ቡድኖች አጭር ምልከታ ( ምድብ አራት)
በረከት ፀጋዬ ምድብ አራት ግብፅ፣ ናይጄሪያ፣ ሱዳን፣ ጊኒ ቢሳው ተሳትፎ፡ 25ኛ ጊዜ ምርጥ ውጤት: ሻምፒዮን (1957፣59፣86፣98፣2006፣08፣10) አሰልጣኝ፡ ካርሎስ ኬሮዥ ኮከብ ተጫዋች፡ ሞሃመድ ሳላህ ምን ይጠብቃሉ፡ ግብፅ የአፍሪካ ዋንጫ የምንጊዜውም ውጤታማ ቡድን…
የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ ብሄራዊ ቡድኖች አጭር ምልከታ ( ምድብ ሶስት)
በረከት ፀጋዬ ምድብ ሶስት ሞሮኮ፣ ጋና፣ ጋቦን፣ ኮሞሮስ ሞሮኮ ተሳትፎ፡ 18ኛ ጊዜ ምርጥ ውጤት፡ ሻምፒዮን (1976) አሰልጣኝ፡ ቫሂድ ሃሊልሆድዚች ኮከብ ተጨዋች፡ አሽራፍ ሃኪሚ ምን ይጠብቃሉ፡ ከ2019 የአፍሪካ ዋንጫ ጥሎ ማለፍ ስንበት መልስ ወደ…
የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ ብሔራዊ ቡድኖች አጭር ምልከታ ( ምድብ 2)
በረከት ፀጋዬ ምድብ ሁለት ሴኔጋል፣ ጊኒ፣ ዚምባቡዌ፣ ማላዊ ሴኔጋል ተሳትፎ፡ 16ኛ ጊዜ ምርጥ ውጤት፡ የፍፃሜ ተፋላሚ (2002፣ 2019) አሰልጣኝ፡ አሊዩ ሲሴ ኮከብ ተጨዋች፡ ሳይዶ ማኔ ምን ይጠብቃሉ፡ የቴራንጋ አንበሶቹ አሁንም የውድድሩ ከፍተኛ ተገማች…
የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ ብሄራዊ ቡድኖች አጭር ምልከታ ( ምድብ 1)
በረከት ፀጋዬ 33ተኛው ቶታል ኢነርጂስ አፍሪካ ዋንጫ በካሜሩን አስተናጋጅነት ከጥር 1-29 ይካሄዳል። አስተናጋጇ ሃገር ዋንጫውን በሃገራቸው ለማስቀረት ይፈልጋሉ። ለ33 ጨዋታዎች ያህል ያለመሸነፍ ጉዞ ላይ ያሉትና የወቅቱ የአፍሪካ ሻምፒዮኖች አልጄሪያ ቢያንስ…









