ሞ ሳላህ ላይ እየተሰጡ ያሉ ትችቶች እንዴት ይታያሉ? 

ግብጻዊው የሊቨርፑል የፊት መስመር ተጫዋች ሞ ሳላህ ከሊዲሱ ጨዋታ መልስ በሰጠው አስተያየት መነጋገሪያ ሆኖ ከርሟል፡፡ 

“ 90 ደቂቃ ሙሉ ተጠባባቂ ወንበር ላይ መሆኔን ላምን አልችልም፡፡ ለሶስተኛ ተከታታይ ጨዋታ ነው ይህ የሆነው፡፡ በእግር ኳስ ዘመኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ይመስለኛል፡፡ ላለፉት አመታት ለዚህ ክለብ በርካታ ነገሮችን አድርጌያለሁ በተለይም ደግሞ ያለፈው አመት” በማለት ነበር ሳላህ ከሊድስ ጨዋታ በኋላ ለጋዜጠኞች አስተያየቱን የሰጠው፡፡ 

ሳላህ ለ7 ደቂቃ ያህል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ለሊቨርፑል ውጤት አለመሳካት እርሱን ተጠያቂ ለማድረግ የፈለገ ሰው እንዳለ ተናግሯል፡፡ ከአሰልጣኙ አርነ ስሎት ጋር ያላቸውን ግንኙነት የተቸ ሲሆን ከዛም በተጨማሪ እንደጄሚ ካራገር ካሉ ተንታኞች ሊሰነዘርበት የሚችለውን ትችት አስቀድሞ ተናግሯል፡፡ 

ሳላህ አያይዞም ከዚህ በፊት ሀሪ ኬን ጋር በተገናኘ ተፈጥሮ ስለነበረው ሁኔታ ተናግሯል፡፡ እርሱ በዛ ቦታ ቢሆንም ሊደርስበት ይችል የነበረውን ትችት እና ተቃውሞ አያይዞ ገልጿል፡፡ 

ከሳላህ አስተያየት በኋላ በርካታ የሚዲያ ሰዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል አየርላንዳዊው የቀድሞው የሊቨርፑል ተጫዋች ጄሰን ማከቲር ይገኝበታል፡፡ ማከቲር ሳላህ ሊቨርፑል ተሸክሞ እንደማያውቅ እና ክለቡን የተሸከመ ተጫዋች ይጠቀስ ቢባል ስቴቨን ጄራርድ ምሳሌ መሆኑን ጠቅሷል፡፡ ሳላህ የሚወደስ ከሆነም እንደጆርዳን ሄንደርሰን አይነት ተጫዋቾች መነሳት እና መደነቅ አለበት በማለት ተናግሯል፡፡ 

ጄሚ ካራገርም እንደተጠበቀው በስካይ ስፖርት ‘Monday Night Football’ ፕሮግራሙ ላይ ሳላህ ከሊቨርፑል በፊት ይህ ነው የማይባል ተጫዋች እንደሆነ ተናግሯል፡፡ ከሊቨርፑል በፊት ሳላህ የሚታወቀው በቻልሲ ያልተሳካለት ተጫዋች በመባል ነው ያለው ካራገር ከዚህም በተጨማሪ ከሀገሩ ግብጽ ጋር እንኳን ዋንጫን አላሸነፈም ብሏል፡፡ 

ከበርካታ ስፍራዎች ሳላህ ትችቶች ገጥመውታል፡፡ ምናልባትም አነጋጋሪው መግለጫ ሲሰጥ ይህ ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል፡፡ ነገር ግን የተሰጡት አስተያየቶች በጣም የተጋነኑ እና መስመርን የሳቱ ይመስላሉ፡፡ 

አብዛኞቹ አስተያየቶች ሳላህ ከዚህ በፊት በቂ ግልጋሎትን እንዳልሰጠ የሚያስመስሉ እና ያሳያቸውን ድንቅ እንቅስቃሴዎች የዘነጉ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ከማከቲር እና ካራገር አስተያየቶችም መረዳት የምንችለው ይህንን ነው፡፡ 

ሳላህን ሙሉ በሙሉ ጫና ውስጥ መክተት እና ስሙን ማጠልሸት የሚመስሉ አስተያየቶችን አስተውለናል፡፡ ሳላህ ሊቨርፑል ከ30 አመታት በኋላ ላሳኩት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ እንደዚሁም ከ14 አመታት በኋላ ላስመዘገቡት የቻፒዮንስ ሊግ ድል ወሳኙን ሚና ተጫውቷል፡፡ 

ሳላህ ባለፉት አመታት ሊቨርፑል ካሳካቸው ድል ጋር ስሙ ጎን ለጎን የሚነሳ ተጫዋች ነው፡፡ እርግጥ ነው የአሰልጣኝን ውሳኔ ማክበር እና ለቡድን አጋሮቹ አክብሮትን ማሳየት ግዴታው ነው፡፡ በእርሱ ላይ የተነሱ አብዛኞቹ አስተያየቶች ግን ምክንያታዊነትን የተከተሉ አይመስሉም፡፡

ለምሳሌ ያህል በዘንድሮው የውድድር ዘመን ያደረጋቸውን እንቅስቃሴዎች ብንመለከት ሳላህ ከየተኛው የሊቨርፑል ተጫዋች የበለጠ በርካታ እድሎችን እንደፈጠረ ኦፕታ ያሳያል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በፍጹም ቅጣት ምት ሳጥን ውስጥ በርካታ ኳሶችን አቀብሏል፡፡ በሌሎች የማጥቃት ንጻሬዎች ፊት ላይ እንዲቀመጥ የሚያደርጉ ቁጥሮች አሉት፡፡ በመከላከሉ ረገድም ከሌላኛው የክንፍ ተጫዋች ኮዲ ጋክፖ ይልቅ በርካታ የሜዳ ክልልን ሸፍኗል፡፡ ስለዚህ ተጠባባቂ ወንበር ላይ እርሱን ለማስቀመጥ ሆነ የሊቨርፑል ውጤት ማጣት የእርሱ ጥፋት ነው ለማለት በቂ መረጃ የለም፡፡ እየተሰነዘሩ ያሉት ትችቶች አግባብ አይደሉም የሚባለው ከዚህ በመነጨ ነው፡፡

Brook Genene

Brook is a football writer who focuses on sports injuries. He has previously written on local sports for Soccer Ethiopia and Ethiopian Business Review magazine.

Related Posts

ጆን ቴሪ በቼልሲ ጊዜያዊ አሰልጣኝነት ምርጫ ማዘኑን ገልጿል

የቀድሞው የቼልሲ የመሀል ተከላካይ ጆን ቴሪ ጥር ላይ በተሰናበቱት አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ምትክ የጊዜያዊ አሰልጣኝነት እድል ባለማግኘቱ ደስተኛ እንዳልሆነ ገልጿል፡፡  ጆን ቴሪ በቼልሲ አካዳሚ በበጎ ፈቃድ አሰልጣኝነት በወር ሁለት ቀን…

ከራባት እስከ አጋዲር፡ AFCON 2025ን የሚያስተናግዱ ዘጠኝ ስታዲየሞች

በበረከት ጸጋዬ ሞሮኮ የ AFCON 2025 ን በስድስት አስተናጋጅ ከተሞች ውስጥ ባሉ ዘጠኝ ስታዲየሞች እያስተናገደች ነው፣ ይህም የአገሪቱንዘመናዊ እና የተለያየ የእግር ኳስ መሠረተ ልማት አጉልቶ ያሳያል። ቀጣዩ አጭር ዳሰሳ ለውድድሩ…

You Missed

Ethiopia Bunna appoints new chairman 

Ethiopia Bunna appoints new chairman 

Diribe Welteji banned for two years

Diribe Welteji banned for two years

ጆን ቴሪ በቼልሲ ጊዜያዊ አሰልጣኝነት ምርጫ ማዘኑን ገልጿል

ጆን ቴሪ በቼልሲ ጊዜያዊ አሰልጣኝነት ምርጫ ማዘኑን ገልጿል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አዲስ አሰልጣኝ አግኝቷል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አዲስ አሰልጣኝ አግኝቷል

ከራባት እስከ አጋዲር፡ AFCON 2025ን የሚያስተናግዱ ዘጠኝ ስታዲየሞች

ከራባት እስከ አጋዲር፡ AFCON 2025ን የሚያስተናግዱ ዘጠኝ ስታዲየሞች

የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ዳሰሳ

የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ዳሰሳ