የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በተደረገው የሴካፋ የማጣሪያ ውድድር ሶስተኛ ሆኖ ጨርሷል።
በደረጃ ጨዋታው ኬንያን 3-0 ያሸነፉት ቀይ ቀበሮዎቹ በቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት በሞሮኮ ለሚደረገው የካፍ ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።
በአፍሪካ መድረክ እስከ 10ኛ የሚወጡ ከሆነም በካታር አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የፊፋ ከ17 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ማለፍ ይችላሉ።
ፊፋ ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫን ከዘንድሮ ጀምሮ በየዓመቱ እንዲካሄድ መወሰኑ ይታወሳል።





