ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች የ4 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አበረከተ

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ‘ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ’ በተሰኘው የ2018 ሶፊማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለምአቀፍ 10ኪ.ሜ. የበጎ አድራጎት ዘመቻው አማካኝነት ያሰባሰበውን 4 ሚሊዮን ብር በቼሻየር ኢትዮጵያ መናገሻ ቢሮ በተከናወነ ደማቅ ስነ-ስርዓት ለተመረጡ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች አስረክቧል።

በዘንድሮው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ድጋፍ የተደረገላቸው ተቋማት ቼሻየር ኢትዮጵያ፣ ተስፋ ማህበራዊና ልማት ማህበር ፣ የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌደሬሽን እና እዘነት አካል ጉዳተኞች ህፃናት እና ወላጆች መርጃ ድርጅት በኢትዮጵያ ናቸው።

​በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ባስተላለፉት መልዕክት “ዛሬ ማዕከሉን ተገኝቼ በመጎብኘቴ በጣም ደስ ብሎኛል ፤ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከስፖርታዊ እንቅስቃሴው ባሻገር ህዝብን ከማስተሳሰር ባለፈ፣ ችግረኞችን ለመርዳት የሚያደርገው ጥረት ለሌሎችም አርአያ የሚሆን ተግባር ነው።በቀጣይም ሌሎች በርካታ ተቋማትን ማገዛችንን እንቀጥላለን” ብለዋል።

​አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ በበኩሉ “ይህን ‘ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ’ ዘመቻን ስንጀምር ዓላማችን ስፖርታዊ ውድድሩ ለወገኖቻችን መድረሻ እንዲሆን ነበር። ዛሬ ላይ በየአመቱ ተጠናክሮ መቀጠሉ አስደሳች ነገር ነው። ከምንሰበስበው ገንዘብ በላይ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶቹ በሚሰጠው ትኩረት ትልቅ ኩራት ይሰማኛል” ሲል ገልጿል።

​በዕለቱ በግላቸው ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ላሰባሰቡና ለዘመቻው ስኬት ጉልህ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ግለሰቦች ልዩ ዕውቅና ተሰጥቷል። ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ወደፊትም ስፖርትን ከበጎ አድራጎት ጋር በማስተሳሰር ማህበራዊ ግዴታውን መወጣቱን እንደሚቀጥልም በዚሁ ወቅት ተገልጿል።

​ይህ ‘ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ’ የተሰኘው ዘመቻ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድርን ከማዘጋጀት ባሻገር ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከሚወጣባቸው መንገዶች ዋነኛው ሲሆን፤ ከተጀመረም 20 ዓመታትን አስቆጥሯል። ባለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት ውስጥ ብቻ ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ከተለያዩ ድርጅቶችና ግለሰቦች በማሰባሰብ ለተለያዩ ተቋማት ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል። ዘመቻው ከገንዘብ ድጋፍ ባለፈ ተቋማቱ ተከታታይ የድጋፍ ምንጭና የመገናኛ ብዙኃን ሽፋን እንዲያገኙ በማድረግ ለህጻናት፣ ለሴቶች፣ ለአካል ጉዳተኞችና ለተፈናቃዮች የላቀ ፋይዳ ያለው ስራ ሲያከናውን ቆይቷል።

Girmachew Kebede

Founder of Tilafok.com, Girmachew Kebede is a sports journalist with more than a decade of newsroom and on-air experience. He served as Deputy Editor-in-Chief at Ethio-Sport newspaper, was host and News Editor for the Bisrat Sport radio show, and worked as a football analyst with Kuas Meda. He co-created the Rigore sports show. He was also sports and political stringer for Voice of America’s Horn of Africa Service. His articles were selected among the Top 10 in Africa by the AIPS Sport Media Awards in 2018 and 2022.

Related Posts

ባንክ ኦፍ አሜሪካ የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. የስያሜ አጋር ሆነ

ከመጋቢት 2019 (March 2027) ጀምሮ ባንክ ኦፍ አሜሪካ ከአፍሪካ ትልቆቹ የሴቶች-ብቻ ሩጫ ውድድሮች አንዱ የሆነው ውድድር የስያሜ አጋር (Presenting Partner) ይሆናል። ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከባንክ ኦፍ አሜሪካ ጋር እያሳደገ የሚገኘው…

Diribe Welteji banned for two years

The Court of Arbitration for Sport (CAS) has partially upheld an appeal by World Athletics against the Ethiopian National Anti-Doping Office (ETH-NADO) and middle-distance runner Diribe Welteji Kejelcha (Ethiopia). Ms…

You Missed

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች የ4 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አበረከተ

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች የ4 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አበረከተ

ባንክ ኦፍ አሜሪካ የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. የስያሜ አጋር ሆነ

ባንክ ኦፍ አሜሪካ የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. የስያሜ አጋር ሆነ

Ethiopia Bunna appoints new chairman 

Ethiopia Bunna appoints new chairman 

Diribe Welteji banned for two years

Diribe Welteji banned for two years

ጆን ቴሪ በቼልሲ ጊዜያዊ አሰልጣኝነት ምርጫ ማዘኑን ገልጿል

ጆን ቴሪ በቼልሲ ጊዜያዊ አሰልጣኝነት ምርጫ ማዘኑን ገልጿል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አዲስ አሰልጣኝ አግኝቷል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አዲስ አሰልጣኝ አግኝቷል