የፌዴሬሽኖች ምርጫ ከግለሰብ በላይ እንዲሆን. . .

  • Opinion
  • December 18, 2024
  • 0 Comments

ሰሞኑን በፌዴሬሽኖች የፕሬዚደንት እና የስራ አስፈፃሚ ምርጫዎች አወዛጋቢ ጉዳዮች ሲነሱ ተመልክተናል። በእርግጥ አንደኛው ተወዳዳሪ ከሌላኛው በችሎታ የተሻለ ስለሚሆን ባለው የስፖርት አደረጃጀት ውስጥ እገሌ ከእገሌ የተሻለ ለውጥ ማምጣት ይችላል። ሆኖም ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት ለተወዳዳሪዎቹ አስቸጋሪ እንደሚሆን አልጠራጠርም። ስለዚህ ትኩረታችን በሁለት ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ቢሆን የተሻለ ይመስለኛል።

የስፖርት አስተዳደር በሁለት ምሶሶዎች የቆመ ነው። በራስ-ገዝነት እና ቅቡልነት ላይ!

  1. ለፌዴሬሽኖች ራስ ገዝ መሆን ከፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖዎች በተቻለ መጠን ነፃ ሆኖ መንቀሳቀስ ማለት ነው። ይህ ራስ-ገዝነት በሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ህጎች ስር የስፖርት ፌዴሬሽኖች የራሳቸውን ደንቦች ከፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች ነፃ ሆነው ማውጣት፣ ማሻሻልና መለወጥን፤ ከመንግስታዊም ሆነ ከሌላ ሶስተኛ ወገን ነፃ ሆነው የራሳቸውን መሪዎች መምረጥን እና ገንዘባቸውን እና የሰው ኃይላቸውን ያለማንም ጣልቃገብነት ለዓላማዎቻቸው ማዋልን ይጨምራል።
    አሁን ባለን የስፖርት አደረጃጀት በአብዛኛዎቹ ጉዳዮች ፌዴሬሽኖቻችን ራስ ገዝ ናቸው ወይም ራሳቸውን በራሳቸው ያስተዳድራሉ ለማለት አልደፍርም። ይህም የሚመነጨው የፌዴሬሽኖቹ የስልጣን ባለቤት ከሆነው ጠቅላላ ጉባዔ አወቃቀር ነው። አብዛኞቹ የጠቅላላ ጉባዔ አባላት በወረዳ፣ በዞን፣ በክልል/ከተማ አስተዳደር ወይም በፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በመሆናቸው ድምፅ ሲሰጡም ሆነ ደንቦችን ሲያፀድቁ ከመንግስታዊ ጣልቃገብነት ነፃ የሚሆኑ አይመስልም። ስለዚህ የጠቅላላ ጉባዔ አባላት ማነንት እና አወቃቀር እስካልተቀየረ ድረስ ነፃ የሆነ የፌዴሬሽኖች ምርጫ ሊኖር አይችልም።
  2. ሁለተኛው የስፖርት አስተዳደር ምሶሶ ቅቡልነት ነው። ይህ ከህጋዊ ቅቡልነት ባለፈ ማህበረሰባዊ ቅቡልነትን ይጨምራል። ለምሳሌ ፊፋ በሴፕ ብላተር ዘመን በሙስና እንደተዘፈቀ ሲታወቅ በእግር ኳስ ተከታታዩ ተቀባይነትን አጥቶ እንደነበር ይታወሳል። ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴም የተቀባይነት እጦት አጋጥሞት ያውቃል። ይህን ለማስተካከልም የስነ-ምግባር እና የመልካም አስተዳደር መርሆችን እና መመሪያዎችን አውጥተዋል። አሻሽለዋል። በሀገር ውስጥ ስንቶቹ ፌዴሬሽኖች በማህበረስቡ ዘንድ ቅቡል እንደሆኑ አንባቢ ይፍረድ። ቅቡልነት የሌላቸው ፌዴሬሽኖች ስፖንስር ማምጣት፣ ገበያ መፍጠር እና አዳዲስ ነፃ የሆኑ ደረጃቸው ላቅ ያለ ብዙ ሰዎችን ወደ ስፖርቶቹ መሳብ ሊቸገሩ ይችላሉ። ይህን መቀየር ሌላ ትልቅ የቤት ስራ ነው።

ራስ-ገዝ ባልሆኑ እና ማህበረሰባዊ ተቀባይነታቸው ጥያቄ ምልክት ውስጥ በገባ ፌዴሬሽኖች በሚደረግ ምርጫ ከግለሰቦች ውድድር ባለፈ የስፖርት ማህበራት አደረጃጀትን መቀየር ዋና አጀንዳ እንዲሆን መወትወት ያስፈልገናል።

  • Girmachew Kebede

    Founder of Tilafok.com, Girmachew Kebede is a sports journalist with more than a decade of newsroom and on-air experience. He served as Deputy Editor-in-Chief at Ethio-Sport newspaper, was host and News Editor for the Bisrat Sport radio show, and worked as a football analyst with Kuas Meda. He co-created the Rigore sports show. He was also sports and political stringer for Voice of America’s Horn of Africa Service. His articles were selected among the Top 10 in Africa by the AIPS Sport Media Awards in 2018 and 2022.

    Related Posts

    ለ25 ዓመታት የተገነባ ራዕይ:- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያና ብሄራዊ ፋይዳው

    (በዶ/ር ጋሻው ዘርጋው አብዛ) የ25ኛ ዓመቱን ያከበረው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ባለፈው ዕሁድ በደመቀ እና በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል። የዚህ ተቋም የ25 ዓመት ጉዞው ብሄራዊ አንድምታ ጥልቅ እና ዘርፈ ብዙ ነው። ታሪካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣…

    የሁለት ዝግጅቶች ወግ

    የቶኪዮው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና የሴቶች የ10000ሜ የወርቅ ሜዳልያ ባለቤቷ ቢያትሪስ ቼቤት ከአራት ሳምንታት በፊት በዳይመንድ ሊግ 1500ሜ ሮጣለች። ቼቤት በተለምዶ የ1500ሜ ራጭ አይደለችም። በኬንያ ሻምፕዮና፡ የጦር ሰራዊቱ ውድድር ወይም ለዓለም…

    Leave a Reply

    You Missed

    Ethiopia Bunna appoints new chairman 

    Ethiopia Bunna appoints new chairman 

    Diribe Welteji banned for two years

    Diribe Welteji banned for two years

    ጆን ቴሪ በቼልሲ ጊዜያዊ አሰልጣኝነት ምርጫ ማዘኑን ገልጿል

    ጆን ቴሪ በቼልሲ ጊዜያዊ አሰልጣኝነት ምርጫ ማዘኑን ገልጿል

    የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አዲስ አሰልጣኝ አግኝቷል

    የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አዲስ አሰልጣኝ አግኝቷል

    ከራባት እስከ አጋዲር፡ AFCON 2025ን የሚያስተናግዱ ዘጠኝ ስታዲየሞች

    ከራባት እስከ አጋዲር፡ AFCON 2025ን የሚያስተናግዱ ዘጠኝ ስታዲየሞች

    የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ዳሰሳ

    የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ዳሰሳ