የሁለት ዝግጅቶች ወግ

የቶኪዮው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና የሴቶች የ10000ሜ የወርቅ ሜዳልያ ባለቤቷ ቢያትሪስ ቼቤት ከአራት ሳምንታት በፊት በዳይመንድ ሊግ 1500ሜ ሮጣለች።

ቼቤት በተለምዶ የ1500ሜ ራጭ አይደለችም። በኬንያ ሻምፕዮና፡ የጦር ሰራዊቱ ውድድር ወይም ለዓለም ሻምፕዮና ማጣሪያ ካልሆነ በስተቀር ደጋግማ የምትሮጠው ውድድር አይደለም።

የዓለም አትሌቲክስን በዚህ ርቀት አትሌቷ ያስመዘገበችውን ምርጥ 10 ፈጣን ሰዓት ብትጠይቁት የሚሰጣችሁ ስድስት በይፋ የተመዘገቡ ውድድሮችን ነው።

ከወር በፊት ግን በዳይመንድ ሊግ 1500ሜ ከጉዳፍ ፀጋይ ጎን ተሰለፈች። ከአራት ደቂቃ በታች ሮጠች። ለ10000ሜ ተዘጋጀች። ምክንያቱም ብዙዎቻችን እንደምናስበው ጉዳፍ በተለምዶ የ1500ሜ ሯጭ ስለሆነች አራት ዙር አካባቢ ሲቀር ዙሩን አፍጥና ውድድሩን የ1500ሜ ፍልሚያ ታደርገዋለች የሚል ነበር። ቼቤት ያሰበችውም ይህን ነው።

ጉዳፍ ዙሩን ለማፍጠን የሞከረችው ግን 1000ሜ ሲቀር ነው። ከውድድሩ በኋላ በሰጠችው አስተያየትም “ዘጠኝ ኪ.ሜ. ላይ ውድድሩን ተቆጣጥሬው ነበር። ከዚያ ለመፍጠን ሞከርኩ። የታክቲክ ስህተት አይደለም” ያለችውም ለእዚህ ነው።

በአካል ብቃት ለፈጣን አጨራረስ ዝግጁ እንደነበረች ብትናገርም ለማፈትለክ ያደረገችው ሙከራ አልተሳካም። ምቾት የነሳት ነገር እንደነበር ግልፅ ነው። ጉዳፍ ምክንያቱን ስታስረዳ “ለሞቃት አየር ፀባይ ብዘጋጅም ወበቁ ያልጠበኩት ነበር” ብላለች ።

ይህ ሁሉ ሲሆን ቼቤት ምቾት ላይ ነበረች። ምክንያቱም በ10000ሜ ውስጥ ራሷን ለ1500ሜ ፍልሚያ አዘጋጅታለች።

“ከባድ እና በጣም ታክቲካዊ ውድድር ነበር። የመጨረሻውን 800ሜ የሮጥኩት በኃይል ነው። ጉዳፍ ከባድ ጫና ብታሳርፍብኝም መፋለም ነበረብኝ። (በዳይመንድ ሊግ) 1500ሜ ሮጫለሁ። ስለዚህ በአዕምሮዬ የ1500ሜ ውድድር ላይ ነበርኩ” በማለት ቼቤት የዳይመንድ ሊግ ዝግጅቷ እንዴት እንደጠቀማት ከውድድሩ በኋላ ተናግራለች።

ለአሰልጣኞቻችን ትልቁ ጥያቄ የሚመጣው እዚህ ላይ ነው። ቼቤት የተጋጣሚ ትንተና ሰርታለች። ለዚህም ተዘጋጅታለች። ጉዳፍ ለምትጠይቃት ጥያቄዎች ሁሉ የኬንያዊቷ አሰልጣኝ መልስ አዘጋጅቶላታል።

የጉዳፍ አሰልጣኝስ? ለሁሉም ሁናቴዎች ምላሽ ተዘጋጅቶ ነበር? ወይስ ዝግጅቱ በአትሌቷ ጥረት እና ተሰጥኦ ላይ ብቻ የተመሰረተ ነው?

(ይህ ፅሁፍ ጉዳፍን ለመውቀስ የተፃፈ አይደለም። አትሌቶቻችን በትንሽ እገዛ፣ በብዙ ልፋት እና ፈተና ከታላላቆች ጋር እንደሚፋለሙ ግልፅ ነው። ሆኖም ባለፉት ዓመታት ብዙ እንደተባለው ስልጠናና የውድድር ዝግጅታችንን መፈተሽ እንደሚገባን የዛሬው ፉክክር እና የሩጫ በኋላ አስተያየት ልዩ ምሳሌ ነው)

Girmachew Kebede

Founder of Tilafok.com, Girmachew Kebede is a sports journalist with more than a decade of newsroom and on-air experience. He served as Deputy Editor-in-Chief at Ethio-Sport newspaper, was host and News Editor for the Bisrat Sport radio show, and worked as a football analyst with Kuas Meda. He co-created the Rigore sports show. He was also sports and political stringer for Voice of America’s Horn of Africa Service. His articles were selected among the Top 10 in Africa by the AIPS Sport Media Awards in 2018 and 2022.

Related Posts

የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ ሩጫ ምዝገባ ዛሬ በይፋ ተጀመረ።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዛሬ የ2019 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ 10 ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ ሩጫ ምዝገባን በይፋ አስጀምሯል። ውድድሩ እሑድ ህዳር 13 ቀን 2019 ዓ.ም. የሚካሄድ ሲሆን፣ በዚህ ዓመት በታሪኩ ከፍተኛውን 60,000…

የጀርመን ስንብት ሲቃኝ

የጀርመን ብሄራዊ ቡድን ከ2026ቱ የአለም ዋንጫ በፓራጏይ 4-3 በፍፁም ቅጣት ምት ተረቶ ተሰናብቷል::  በዚህም መሀል አሰልጣኝ ጁሊያን ናግልስማን ከባድ ትችት እየገጠመው ነው::  የቀድሞው የጀርመን እና አርሰናል ግብ ጠባቂ የንስ ሌማን…

You Missed

የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ ሩጫ ምዝገባ ዛሬ በይፋ ተጀመረ።

የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ ሩጫ ምዝገባ ዛሬ በይፋ ተጀመረ።

Senaf Wakuma joins Simba Queens in Tanzania

Senaf Wakuma joins Simba Queens in Tanzania

የጀርመን ስንብት ሲቃኝ

የጀርመን ስንብት ሲቃኝ

Gudaf Tsegay banned for four months

Gudaf Tsegay banned for four months

Ethiopia U17 to Face Mozambique in World Cup Play-Off

Ethiopia U17 to Face Mozambique in World Cup Play-Off

Ethiopia Learns Fate in AFCON 2027 Qualification Draw

Ethiopia Learns Fate in AFCON 2027 Qualification Draw