ፕሪሚየር ሊግ ወይንስ ሱፐር ሊግ? 

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በክረምቱ ዝውውር ከ3 ቢሊዮን ፓውንድ በላይ አውጥተዋል:: 

በትላንትናው እለት በተጠናቀቀው የክረምት የዝውውር መስኮት የእንግሊዝ ክለቦች በከፍተኛ   ልዩነት ከሌሎች ሊጎች በላይ ለዝውውር ገንዘብ አውጥተዋል:: 

ከዚህ በፊት በ2022-23 የውድድር ዘመን ተመዝግቦ ከነበረው የ2.7 ቢሊዮን ፓውንድ ወጪ የዘንድሮው ልቆ ተገኝቷል:: ይህም ማለት 20ዎቹ ክለቦች ከዚህ በፊት ከነበረው ከፍተኛ ወጪ 650 ሚሊዮን ፓውንድ የበለጠ አውጥተዋል:: 

የወጪ እና ገቢ ልዩነት ሲሰላ 1.2 ቢሊዮን ፓውንድ ሲሆን ይህም ከፍተኛው መጠን ሆኖ ተመዝግቧል:: 

እንደሮይተርስ ዘገባ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ወጪ አምስቱ ታላላቅ ሊጎች የሚባሉት ስፔን ጣሊያን ጀርመን እና ፈረንሳይ ካወጡት አንፃር የ51% ድርሻ ይዟል:: 

ምንም እንኳን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ትርፍ ላይ የተመሰረተ ጥብቅ የፋይናንስ ህግ ቢኖረውም የክለቦቹ ከፍተኛ ወጪ ማውጣት መቻል የቴሌቭዥን ገቢያቸውን ከፍተኛነት የሚያሳይ ነው ተብሏል:: 

Brook Genene

Brook is a football writer who focuses on sports injuries. He has previously written on local sports for Soccer Ethiopia and Ethiopian Business Review magazine.

Related Posts

ፖል ቴርጋት በ2026 ግራንድ አፍሪካን ረን ላይ የክብር እንግዳ ሆኖ ይሳተፋል

via Great African Run ዋሽንግተን ዲሲ:- ዝነኛው የኬንያ የረጅም ርቀት ሯጭ ፖል ቴርጋት ኦክቶበር 10 ቀን 2026 በአሌክሳንድሪያ፣ ቨርጂኒያ በሚካሄደው ግራንድ አፍሪካን ረን የክብር እንግዳ ሆኖ እንደሚሳተፍ አዘጋጆቹ አስታወቁ። ፖል…

Ethiopian Addisu Gobena wins Sydney Marathon

Addisu Gobena wins Sydney Marathon with course-record performance Ethiopian athlete Addisu Gobena won the Sydney Marathon on Saturday August 30, setting a new course record at the World Athletics Platinum Label event.…

You Missed

ፖል ቴርጋት በ2026 ግራንድ አፍሪካን ረን ላይ የክብር እንግዳ ሆኖ ይሳተፋል

ፖል ቴርጋት በ2026 ግራንድ አፍሪካን ረን ላይ የክብር እንግዳ ሆኖ ይሳተፋል

Ethiopian Addisu Gobena wins Sydney Marathon

Ethiopian Addisu Gobena wins Sydney Marathon

Isayas Jira has emerged as the sole candidate for the EFF Presidential election 

Isayas Jira has emerged as the sole candidate for the EFF Presidential election 

Abubeker Nassir has joined Mechal

Abubeker Nassir has joined Mechal

Bahir Dar stadium to host AFCON Qualifier between Ethiopia and Senegal

Bahir Dar stadium to host AFCON Qualifier between Ethiopia and Senegal

የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ ሩጫ ምዝገባ ዛሬ በይፋ ተጀመረ።

የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ ሩጫ ምዝገባ ዛሬ በይፋ ተጀመረ።