ሁለቱ የማንችስተር ክለቦችን ጨምሮ 5 ቡድኖች ባለፉት ሶስት አመታት የዋዥቀ አቋምን እንዳሳዩ CryptoCasinos ያወጣው ቁጥራዊ መረጃ ያሳያል::
- ማንችስተር ዩናይትድ
የ20 ጊዜ የፕሪሚየር ሊግ አሸናፊዎቹ ከትልቁ ዋንጫ ከራቁ 12 አመታት ተቆጥረዋል:: ከ2022/23 አንፃር ዩናይትድ 33 ነጥቦች ሲቀንሱ 12 ጨዋታዎችን ሳያሸንፉ ቀርተዋል:: ከዚህም በተጨማሪ ያስቆጠሯቸው ግቦች በ14 አንሰዋል::
2. ቶተንሀም ሆትስፐር
ቶተንሀም በበኩላቸው በ3 የውድድር ዘመናት 22 ነጥቦች ቀንሰዋል:: በእነዚህም ጊዜያት 48 ጨዋታዎችን ተሸንፈዋል::
3. ማንችስተር ሲቲ
ለአራት ተከታታይ አመታት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ማሸነፍ የቻሉት ማንችስተር ሲቲ ሳይቀሩ ባለፉት ሶስት አመታት የአቋም መዋዥቅ አሳይተዋል፡፡ ሲቲ በሶስቱ የውድድር አመታት 251 ነጥቦችን ሰብሰባዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ 77 ጨዋታዎችን አሸንፈዋል፡፡ እንደዛም ሆኖ ግን በ18 ነጥቦች እና 7 ድሎች አንሰው ተገኝተዋል፡፡
4. አርሰናል
ለተከታታይ ሶስት አመታት ሶስተኛ በመሆን ያጠናቀቁት አርሰናል ከአመት አመት ነጥቦቻቸው እየቀነሱ ነው፡፡ በአጠቃላይ 247 ነጥቦች እና 15 ሽንፈቶች ቢያጋጥማችማውም በእነዚህ አመታት በ10 ነጥብ መቀነሳቸው ዋንጫውን እንዳያነሱ ምክንያት ሆኖባቸዋል፡፡
5. ኒውካስል ዩናይትድ
ከዝርዝር ውስጥ ካሉት ከለቦች ኒውካስል ዩናይትድ የተሻለ እንቅስቃሴ አላቸው፡፡ የቀነሱት ነጥብም 5 ብቻ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
ከተጀመረ ሶስተኛ ሳምንት ላይ በደረሰው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሊቨርፑል በክረምቱ ካደረጉት መጠናከር በኋላ ጠንካራ ተፎካካሪ እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡






