ፌዴሬሽኑ እና የሊግ ተሳታፊዎችን ቁጥር ማሳደግ

  • amharic
  • August 12, 2025
  • 0 Comments

ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ሲዳማ ቡና የስፖርት ግልግል ፍርድ ቤት /ካስ/ የፅሁፍ ምልልስ የተረዳሁት ነገር ፌዴሬሽኑ የፕሪምየር ሊግ ክለቦችን 20 ለማድረግ ያቀረበው ምክንያት ምንም አይነት ህጋዊ መሰረት የሌለው መሆኑን ነው::

እንደምታስታውሱት ፌዴሬሽኑ ሊጉን ወደ 20 ክለቦች ለማሳደግ ያቀረበው ምክንያት በፕሪምየር ሊጉ የፋይናንስ አሰራር ተቆጣጣሪ ኮሚቴ ከተመረመሩት እና በኋላም ከተቀጡት አራት ክለቦች ውጭ ያሉት ክለቦች አለመመርመራቸውን እና በክለቦች የክፍያ ስርዓት አስተዳደር መመሪያ መሰረት ከጥፋት ነፃ መሆናቸው አለመረጋገጡ ነው::

ምስል 1- የፌደሬሽን ምክንያት

ሲዳማ ቡና ለ”ካስ” ባስገባው መከራከሪያ ሌሎቹ ክለቦች አለመመርመራቸውን በምክንያት በማቅረብ ምርመራው በዘፈቀደ የተደረገ መሆኑን ይገልፃል:: በዚህም አራቱ ክለቦች ተለይተው መቀጣታቸው አድሏዊ እና ኢፍትሀዊ [የውድድር] ከባቢ በመፍጠር ሲዳማ ቡና እና ሌሎቹ ሶስት ክለቦች ተገቢ ያልሆነ ኢላማ እንዲሆኑ ተደርገዋል ይላል:: (ምርመራውን ያደረገው ፌዴሬሽኑ እንዳልሆነ ልብ ይሏል)


ፌዴሬሽኑ በምላሹ በክለቦች የክፍያ ስርዓት አስተዳደር መመሪያ መሰረት የፋይናንስ አሰራር ተቆጣጣሪ ኮሚቴው ክለቦችን በዘፈቀደ መርጦ የመመርመር መብት እንዳለው ገልፇል:: ስለዚህ ሲዳማ ቡና እና ሌሎች ሶስት ክለቦች ተለይተው መመርመራቸው እና መቀጣታቸው የህግ ጥሰት እንደሌለበት በፅሁፍ ተከራክሯል::


የእኔ ጥያቄ እዚህ ላይ ነው:: በፌዴሬሽኑ የህግ ምላሽ መሰረት የ14ቱ ክለቦች አለመመርመር ምንም አይነት የህግ ጥሰት ከሌለበት “ገና ለገና አጥፍተው ይሆናል: ነፃ አይሆኑም” በሚል የሊጉን ተሳታፊዎች ቁጥር ማሳደግ የህግ መሰረቱ ምንድን ነው? ክለቦቹ በእግር ኳሱ የፍትህ አካላት ጥፋተኛ እስኪባሉ ድረስ ነፃ መሆናቸውንስ አይቃረንም? ፌዴሬሽኑ ለ”ካስ” የህግ ጥሰት የለም እያለ በሀገር ውስጥ ውሳኔዎቹ ግን ስህተት እንዳለ የሚያሳይ ውሳኔ መወሰኑ አይቃረንም?

Girmachew Kebede

Founder of Tilafok.com, Girmachew Kebede is a sports journalist with more than a decade of newsroom and on-air experience. He served as Deputy Editor-in-Chief at Ethio-Sport newspaper, was host and News Editor for the Bisrat Sport radio show, and worked as a football analyst with Kuas Meda. He co-created the Rigore sports show. He was also sports and political stringer for Voice of America’s Horn of Africa Service. His articles were selected among the Top 10 in Africa by the AIPS Sport Media Awards in 2018 and 2022.

Related Posts

ትዕግስት አሰፋ የራሷን የማራቶን ክብረ ወሰን አሻሽላለች 

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ በለንደን ማራቶን በ2ሰአት 15 ደቂቃ ከ41 ሰከንድ በመጨረስ የራሷን የሴቶች ብቻ ክብረ ወሰን ማሻሻል ችላለች፡፡  ትዕግስት የ3 ጊዜ የኦሎምፒክ አሸናፊዋን ሄለን ኦቢሪ እና የ2021 የለንደን ማራቶችን…

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች የ4 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አበረከተ

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ‘ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ’ በተሰኘው የ2018 ሶፊማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለምአቀፍ 10ኪ.ሜ. የበጎ አድራጎት ዘመቻው አማካኝነት ያሰባሰበውን 4 ሚሊዮን ብር በቼሻየር ኢትዮጵያ መናገሻ ቢሮ በተከናወነ ደማቅ ስነ-ስርዓት ለተመረጡ…

You Missed

Gudaf Tsegay banned for four months

Gudaf Tsegay banned for four months

Ethiopia U17 to Face Mozambique in World Cup Play-Off

Ethiopia U17 to Face Mozambique in World Cup Play-Off

Ethiopia Learns Fate in AFCON 2027 Qualification Draw

Ethiopia Learns Fate in AFCON 2027 Qualification Draw

CBE Crowned Women’s Premier League Champions

CBE Crowned Women’s Premier League Champions

Ethiopia U17 Faces Morocco in Crucial AFCON Encounter

Ethiopia U17 Faces Morocco in Crucial AFCON Encounter

ትዕግስት አሰፋ የራሷን የማራቶን ክብረ ወሰን አሻሽላለች 

ትዕግስት አሰፋ የራሷን የማራቶን ክብረ ወሰን አሻሽላለች