የጀርመን ብሄራዊ ቡድን ከ2026ቱ የአለም ዋንጫ በፓራጏይ 4-3 በፍፁም ቅጣት ምት ተረቶ ተሰናብቷል::
በዚህም መሀል አሰልጣኝ ጁሊያን ናግልስማን ከባድ ትችት እየገጠመው ነው::
የቀድሞው የጀርመን እና አርሰናል ግብ ጠባቂ የንስ ሌማን ናግልስማን ኳስን በትልቅ ደረጃ ተጫውቶ አለማለፉ ለዚህ ምክንያት እንደሆነ አስረድቷል::
” ጥቃቅን ነገሮችን ማየት አልቻለም” በማለትም አሰልጣኙን ተችቷል::
የቀድሞው የሊቨርፑል እና የጀርመን አማካይ ዲዲ ሀማን በበኩሉ ናግልስማን ተጫዋቾቹን አይመለከትም:: በወር ውስጥ አንድ ወይንም ሁለት ጨዋታ ቢያይ ነው በማለት ተናግሯል::
ነገር ግን ችግሩ የአሰልጣኙ ብቻ ነው?
የጀርመን ብሄራዊ ቡድን ከ2014 ጀምሮ የያዘውን የኃሊት ጉዞ ቀጥሎበታል:: በዚህ መሀል ትልቅ ጥያቄ የሚያስነሳው ወሳኝ ተጫዋቾቻቸውን ለመተካት መቸገራቸው ነው:: ሚሮስላቭ ክሎሰ : ፊሊፕ ላህም : ባስቲያን ሽዋንሽታይገር እና ሌሎችም በበቂ ሁኔታ አልተተኩም:: ትላንት የመጨረሻ የብሄራዊ ቡድን ጨዋታውን ያደረገው ኖየር እራሱ በቀላሉ የሚተካ አይመስልም::
የጀርመን የታለንት ፋክተሪ ግን እንደዚህ አልነበረም:: በየጊዜው ወጣት ተጫዋቾችን ይዞ ብቅ የሚል ነበር::
ለምሳሌ እአአ 2009 ላይ የጀርመን ከ21 አመት በታች የአውሮፓ ውድድርን ሲያሸንፍ ኖየር : ሜሱት ኦዚል እና ጄሮም ቦአቲንግ የቡድኑ አካል ነበሩ::
በተመሳሳይ አመት የ17 አመት በታች ቡድኑም ሻምፒዮን ሆኗል::
የጀርመን ከ21 አመት በታች ቡድን በተደጋጋሚ የአውሮፓ ውድድርን በቅርብ አመታት ቢያሸንፍም በቋሚነት ከዛ እርከን ወደዋናው ቡድን የሚያልፉ ተጫዋቾችን ማፍራት ሳይችል ቀርቷል::
በአጠቃላይ የጀርመን talent factory ነጥፏል::
በአንፃሩ ፈረንሳይ በተጫዋች ላይ ተጫዋች እያፈራች ቡድኑን አጥለቅልቃዋለች::
ጁሊያን ናግልስማን ብዙ እንደሚተች ግልፅ ነው:: እውነቱን ለመናገር ግን ባለው ነው መስራት የሚችለው::
ተመሳሳይ ባህሪ ያላቸው ቨርትዝ እና ሙሲዬላ… ከብቃቱ የወረደ ሳኔ… ግብ ፊት sharpness የሚጎለው ሀቨርትዝ… ክፍተቱ ብዙ ነው:: አማራጭ ደግሞ የለም!






