ፖል ቴርጋት በ2026 ግራንድ አፍሪካን ረን ላይ የክብር እንግዳ ሆኖ ይሳተፋል

via Great African Run

ዋሽንግተን ዲሲ:- ዝነኛው የኬንያ የረጅም ርቀት ሯጭ ፖል ቴርጋት ኦክቶበር 10 ቀን 2026 በአሌክሳንድሪያ፣ ቨርጂኒያ በሚካሄደው ግራንድ አፍሪካን ረን የክብር እንግዳ ሆኖ እንደሚሳተፍ አዘጋጆቹ አስታወቁ።

ፖል ቴርጋት በዕለቱ ከዝነኞቹ የኢትዮጵያ አትሌቶች ደራርቱ ቱሉ፣ ጥሩነሽ ዲባባ እና ስለሺ ስህን ጋር በክብር እንግድነት ይገኛል ተብሏል።

ፖል ቴርጋት በዓለም የረጅም ርቀት ሩጫ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ ካላቸው አትሌቶች አንዱ ነው። አምስት ጊዜ የዓለም ክሮስ ካንትሪ ሻምፒዮን ሲሆን በኦሎምፒክ 10,000 ሜትር ሁለት ጊዜ የብር ሜዳሊያ አሸንፏል።
በ10,000 ሜትር፣ በግማሽ ማራቶን እና በማራቶንም የዓለም ክብረወሰን ባለቤት ነበር። በ2003 በበርሊን ማራቶን 2 ሰዓት ከ4 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ በመግባት፣ የማራቶንን ርቀት ከ2 ሰዓት ከ5 ደቂቃ በታች ያጠናቀቀ የመጀመሪያው አትሌት ሆኗል።

ለኢትዮጵያውያን የአትሌቲክስ አድናቂዎች ደግሞ ፖል ቴርጋት ከአትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ጋር ባደረጋቸው እጅግ አጓጊ ፉክክሮች የማይረሳ ስም ነው። በተለይ በ2000 የሲድኒ ኦሎምፒክ የ10,000 ሜትር ፍጻሜ ኃይሌ ገብረሥላሴ ቴርጋትን በ0.09 ሰከንድ ብቻ ቀድሞ ያሸነፈበት ውድድር እስከዛሬ ድረስ በኦሎምፒክ የረጅም ርቀት ሩጫ ታሪክ ውስጥ ከማይረሱ ፉክክሮች አንዱ ነው።

ከውድድር ስኬቱ ባሻገር ፖል ቴርጋት ለስፖርት እድገት፣ ለወጣቶች እና ለማህበረሰብ በሚያደርገው አስተዋጽኦም ይታወቃል።የግራንድ አፍሪካን ረን ዳይሬክተር ዶ/ር ጋሻው አብዛ የፖል ቴርጋትን ተሳትፎ አስመልክተው “ፖል ቴርጋት ከደራርቱ ቱሉ፣ ከጥሩነሽ ዲባባ እና ከስለሺ ስህን ጋር በአንድ ጠዋት ማግኘት ለማህበረሰባችንና በዕለቱ ለሚሳተፉ ሁሉ ትልቅ ክብር ነው” ብለዋል።

ግራንድ አፍሪካን ረን በ2026 ለስምንተኛ ዓመት ይካሄዳል። ዝግጅቱ የአፍሪካ አትሌቶች በአትሌቲክስ፣ በረጅም ርቀት ሩጫ እና በክሮስ ካንትሪ ያስመዘገቡትን አኩሪ ስኬት ለማክበር የተጀመረ ሲሆን ከማንኛውም ማህበረሰብ ለሚመጡ ሁሉ ክፍት ነው።

ባለፉት ሰባት ዓመታት አትሌቶች ቀነኒሳ በቀለ፣ ገንዘቤ ዲባባ፣ መሰረት ደፋር፣ ትዕግሥት አሰፋ እና ጉዳፍ ፀጋይን ጨምሮ በርካታ ዝነኛ አትሌቶች በግራንድ አፍሪካን ረን ተገኝተዋል። የዘንድሮው ግራንድ አፍሪካን ረን ቅዳሜ ኦክቶበር 10 ቀን 2026 በአሌክሳንድሪያ፣ ቨርጂኒያ ይካሄዳል።

ተጨማሪ መረጃ በዚህ ድረ-ገፅ እንደሚገኝ ተጠቁሟል: www.africanrun.com

Girmachew Kebede

Founder of Tilafok.com, Girmachew Kebede is a sports journalist with more than a decade of newsroom and on-air experience. He served as Deputy Editor-in-Chief at Ethio-Sport newspaper, was host and News Editor for the Bisrat Sport radio show, and worked as a football analyst with Kuas Meda. He co-created the Rigore sports show. He was also sports and political stringer for Voice of America’s Horn of Africa Service. His articles were selected among the Top 10 in Africa by the AIPS Sport Media Awards in 2018 and 2022.

Related Posts

Ethiopian Addisu Gobena wins Sydney Marathon

Addisu Gobena wins Sydney Marathon with course-record performance Ethiopian athlete Addisu Gobena won the Sydney Marathon on Saturday August 30, setting a new course record at the World Athletics Platinum Label event.…

Isayas Jira has emerged as the sole candidate for the EFF Presidential election 

The Ethiopian Football Federation has announced that current President Isayas Jira has emerged as the only candidate for the Presidential election set to take place in September.  After reviewing the…

You Missed

ፖል ቴርጋት በ2026 ግራንድ አፍሪካን ረን ላይ የክብር እንግዳ ሆኖ ይሳተፋል

ፖል ቴርጋት በ2026 ግራንድ አፍሪካን ረን ላይ የክብር እንግዳ ሆኖ ይሳተፋል

Ethiopian Addisu Gobena wins Sydney Marathon

Ethiopian Addisu Gobena wins Sydney Marathon

Isayas Jira has emerged as the sole candidate for the EFF Presidential election 

Isayas Jira has emerged as the sole candidate for the EFF Presidential election 

Abubeker Nassir has joined Mechal

Abubeker Nassir has joined Mechal

Bahir Dar stadium to host AFCON Qualifier between Ethiopia and Senegal

Bahir Dar stadium to host AFCON Qualifier between Ethiopia and Senegal

የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ ሩጫ ምዝገባ ዛሬ በይፋ ተጀመረ።

የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ ሩጫ ምዝገባ ዛሬ በይፋ ተጀመረ።