በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረው የአጥቂዎች ዝውውር 

ከጥቂት አመታት በፊት ይህ ነው የሚባል የዘጠኝ ቁጥር ተጫዋች አልነበረም፡፡ ይህም በርካታ ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦችን ያሳስብ ነበር፡፡ በተለይም በ2010ቹ ገነው ከወጡት እንደሉዊስ ስዋሬዝ ፤ ሰርጂዮ አግዌሮ ፤ ካሪም ቤንዚማ ፤ ሮበርት ሌቫንዶቭኪ እና ኤዲንሰን ካቫኒ በሃላ ልዩ ችሎታ ያለው እና ማራኪ አጥቂ ለማግኘት አስቸጋሪ ሆኗል፡፡ በርካታ ክለቦችም አይናቸውን እንግሊዛዊው ሀሪ ኬን ላይ አድርገው ነበር፡፡ እርሱ ግን ከተጠበቀው በላይ ቆይታውን በቶተንሀም አድርጓል፡፡ ማንችስተር ሲቲ እርሱን ለማስፈረም ያልፈነቀለውን ድንጋይ ልብ ይሏል፡፡

በእነዚህ ጊዜያቶች ውስጥ አርሰናል ፒየር ኤመሪክ አውባሜያንግ እና አሌክሳንደር ላካዜትን አስፈርሟል፡፡ ማን ሲቲ ያለ አጥቂ የተጫወቱበት የውድድር ዘመን ነበር ( 2021/22)፡፡ ቼልሲ አልቫሮ ሞራታን ሲሞክሩ ማንችስተር ዩናይትድ ለሮሜሉ ሉካኩ እድልን ሰጥተዋል፡፡ 

በአሁኑ የክረምት የዝውውር መስኮት ነገሮች የተቀያየሩ ይመስላሉ፡፡ ማንችስተር ዩናይትድ ቤንጃሚን ሼሽኮን ከላይፕዚሽ አስፈርሟል፡፡ ቼልሲ ጆዋአ ፔድሮ እና ሊያም ዴላፕን አክሏል፡፡ ሊቨርፑል ሁጎ ኢኪቲኬን እና አርሰናል ደግሞ ቪክቶር ዮኮሬስን የግላቸው አድርገዋል፡፡ 

የሊቨርፑል ቢዝነስ ግን አላለቀም፡፡ የኒውካስል ዩናይትዱን አሌክሳንደር ኢሳክ ይፈልጋሉ፡፡ ኒውካስል በበኩላቸው ስትራድ ላርሰንን ከዎልቭስ ዋልተማደን ከሽቱትጋርት ለማምጣት እየተጉ ነው፡፡ የዊሳም ጉዳይ ገና አላበቃም፡፡ 

ይህ ሁሉ አጥቂ ከየት መጣ? 

እግር ኳስ ተለዋዋጭ ስፖርት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በተለይም አሁን ባለንበት ዘመን ከፍተኛ የሆነ የታክቲክ እና ቴክኒክ ለውጦች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ቀጣዩ ትልቅ revolution አጥቂዎች ላይ የሚያተኩር ይመስላል፡፡

እንደኢኪቲኬ፤ አይዛክ፤ ዋልተማደ እና ጉራሲ አይነት ረጅም ሆነው ከእግር ኳስ ጋር ምቾት የሚሰማቸው ተጫዋቾች ተመራጭ ሆነዋል፡፡ እነዚህ ተጫዋቾች ግብ ማስቆጠር የሚችሉት ከርቀት ወይንም በቅርበት በእግራቸው tap in ብቻ ሳይሆን በግንባራቸውም ጭምር ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ኳስ ምስረታ ላይ የላቀ ሚና አላቸው፡፡ hold play ላይ የላቁ ናቸው፡፡ ይታትራሉ፡፡ ብቻ ምን አለፋችሁ the full package ናቸው፡፡

  • Brook Genene

    Brook is a football writer who focuses on sports injuries. He has previously written on local sports for Soccer Ethiopia and Ethiopian Business Review magazine.

    Related Posts

    የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አዲስ አሰልጣኝ አግኝቷል

    የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌን ቀጣዩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ በመምረጥ ውሳኔ አሳልፏል። አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ በአሁኑ ወቅት የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ ሆነው…

    ኒኮ ዋልተማደ- በወሳኝ ሰአት የተገኘ አጥቂ

    የጀርመን ብሄራዊ ቡድን የ2014ቱን የአለም ዋንጫ ካሸነፉ ማግስት አንድ ከባድ ነገርን መጋፈጥ ነበረባቸው:: ኑሮ ያለድንቁ አጥቂ ሚሮስላቭ ክሎዘ! በአሁኑ ሰአት በጀርመን ሁለተኛ ዲቪዚዮን የቡንደስሊጋ ዋንጫን ብዙ ጊዜ በማሸነፍ ሁለተኛ ላይ…

    You Missed

    Ethiopia Bunna appoints new chairman 

    Ethiopia Bunna appoints new chairman 

    Diribe Welteji banned for two years

    Diribe Welteji banned for two years

    ጆን ቴሪ በቼልሲ ጊዜያዊ አሰልጣኝነት ምርጫ ማዘኑን ገልጿል

    ጆን ቴሪ በቼልሲ ጊዜያዊ አሰልጣኝነት ምርጫ ማዘኑን ገልጿል

    የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አዲስ አሰልጣኝ አግኝቷል

    የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አዲስ አሰልጣኝ አግኝቷል

    ከራባት እስከ አጋዲር፡ AFCON 2025ን የሚያስተናግዱ ዘጠኝ ስታዲየሞች

    ከራባት እስከ አጋዲር፡ AFCON 2025ን የሚያስተናግዱ ዘጠኝ ስታዲየሞች

    የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ዳሰሳ

    የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ዳሰሳ