“Ethiopia doesn’t have many options at number 9” Gebremedin Haile

Ethiopian national team head coach Gebremedin Haile stated that there is a lack of quality number 9s in Ethiopia. The coach was talking to the media after Ethiopia’s two games…

A dull affair between Ethiopia and Sierra Leone ends goalless 

The 2026 World Cup qualifier game between Ethiopia and Sierra Leone ended in a 0-0 draw.  Kenean Markneh on the ball- pic via Ethiopian Football Federation The Ethiopian national team…

ኢትዮጵያ ከሴራሊዮን- ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ

አትዮጵያ በገብረመድህን ኃይሌ ስር የምታደርገው የመጀመሪያው ጨዋታ ይሆናል:: ለ2026 አለም ዋንጫ በሚደረገው ማጣሪያ ኢትዮጵያ ሴራሊዮንን ምሽት 4 ሰዓት ላይ በኤል-አብዲ ስቴዲየምትገጥማለች::  ኢትዮጵያ የአለም ዋንጫ ማጣሪያዋን ሴራሊዮንን በመግጠም ትጀምራለች:: የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በአዲሱ አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሃይሌ እየተመራ የመጀመሪያውን የነጥብ ጨዋታያደርጋል::  ከጅማ አባ ጅፋር እና መቀለ 70 አንደርታ ጋር የፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ መሆን የቻሉት እና ኢትዮጵያ መድንከመጡም በኃላ የተሳካ ቆይታን ያደረጉት አሰልጣኝ ገብረመድን ከውጤት ከራቀ ሰንበትበት ያለውን ብሄራዊቡድን የማንሰራራት ከፍተኛ ኃላፊነት አለባቸው::  የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ደካማ እንቅስቃሴ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን ከምድቡምበ4 ነጥብ መጨረሻ በመሆን ነበር ያጠናቀቀው::  ብሄራዊ ቡድኑ በሰኔ 2022 ግብፅ ላይ ካስመዘገበው ድንቅ ብቃት መልስ በቻን ውድድርም ሆነ በማጣሪያጨዋታዎች ደካማ እንቅስቃሴን አሳይቷል:: ይህም ለአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከኮንትራታቸው መጠናቀቅ ቀደምብሎ ከስራ ለመልቀቅ ምክንያት ሆኗል::  የውበቱ ቡድን ኳስን አዘውትሮ የመቆጣጠር ልምድ ቢኖረውም አደገኛ ክልል ውስጥ ከመገኘት እና እድሎችንከመፍጠር አንፃር ብዙ ጥያቄዎች የሚነሱበት ነበር:: ገብረመድህን በቅድመ ጨዋታ መግለጫቸው ” በራሳችንሜዳ ብዙ የመቆየት ነገር አይኖርም ” በማለት መናገራቸው የተለየ ነገርን ይዘው ለመምጣት እንዳሰቡ ፍንጭንየሰጠ ነበር::  “ከኳስ ውጭ ያለን እንቅስቃሴ በጣም ደካማ ነው ፤ ይሄንንም ለማሻሻል በጣም እየሰራን ነው። ሁሌም ቢሆንኳስ ስናጣ ሁላችንም መሮጥ ይኖርብናል:: ከዚህ አንፃር መጠነኛ ለውጦች ቢኖርም ይበልጥ በጊዜ ሂደት ግፊትአሳድረን የምንሰራበት ከሆነ ሊመጣ ይችላል” በማለትም ምን ላይ አተኩረው ልምምዳቸውን እንደተገበሩገልፀዋል::  ዋልያዎቹ የወሳኝ አጥቂዎቻቸውን ግልጋሎት አያገኙም:: ሽመልስ በቀለ እንደዚሁም ለረጅም ጊዜ ጉዳት ላይየከረመው አቡበከር ናስር አይጫወቱም:: ከዚህ ቀደም እራሱን ከብሄራዊ ቡድን ያገለለው ጌታነህ ከበደበውሳኔው መፅናቱን ለማወቅ ተችሏል::  የባህር ዳሩ አማካይ አለልኝ አዘነ ከቡድኑ ጋር አለመኖር በብዙዎች ዘንድ ጥያቄን ያስነሳ ነበር:: በእርሱ ቦታ ላይያሉት ጋቶች ፓኖም እና ናትናኤል ዘለቀ የተሻለ ብቃት ላይ በመኖራቸው መመረጣቸውን ገብረመድህንተናግረዋል::  ተጋጣሚው ቡድን ሴራሊዮን እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ አልቻሉም:: ለዚህ ጨዋታ ባደረጉትዝግጅት ከቤኒን ጋር አቻ ሲወጡ ሱማሊያን አሸንፈዋል::  ሴራሊዮን በአዲሱ አሰልጣኝ አሚዱ ካሪም እየተመራች ትቀርባለች:: ካሪም ከኢትዮጵያ ከባድ ፉክክርእንደሚጠብቁ እና ተጋጣሚያቸው በቀላሉ እጅ እንደማትሰጥ ተናግረዋል:: 

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ቀጣይ እጣ ፈንታ ምንድን ነው?

ዋልያዎቹ በ4 ነጥብ ከምድባቸው መጨረሻ በማጠናቀቅ አይቮሪ ኮስት ለምታዘጋጀው አፍሪካ ዋንጫ ማለፍ ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ በሀገር ውስጥ ጨዋታን ለማድረግ ያልታደለው ብሄራዊ ቡድን በሜዳም ከሜዳ ውጭም በርካታ ፈተናዎች እየገጠሙት ይገኛሉ፡፡ Picture- Ethiopian…

የአትላስ አናብስት አለምን አስደምመዋል

መቶ ሃያ ደቂቃዎችን ከፈጀ እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ መልስ የአፍሪካ ተወካይ የሆነችው ሞሮኮ ስፔንን በመለያ ምት 3-0 በመርታት የሩብ ፍጻሜ ተፋላሚ መሆን ችላለች፡፡ ይህም ከካሜሩን፤ሴኔጋል እና ጋና በመቀጠል የአለም ዋንጫ ሩብ…

የጀርመን ብሄራዊ ቡድን ችግር ምንድን ነው?

ለሁለተኛ ተከታታይ አለም ዋንጫ የጀርመን ብሄራዊ ቡድን ከምድብ ማለፍ አቅቶት በጊዜ ተሰናብቷል፡፡ ከ2018 በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ከምድብ ሳያልፍ የቀሩት 1938 አ.ም ነበር፡፡ ለረጅም ጊዜያት የውድድሮች የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ የመድረስ ልምድ…

የአለም ዋንጫ ቤተኞች እነማን ናቸው?

by Bereket Tsegaye አለም በጉጉት የሚጠብቀውና የፕላኔታችን ትልቁ የእግር ኳስ ውድድር እንደሆነ የሚታመነው የአለም ዋንጫ በሚጢጢዋና የባህረ ሰላጤዋ እንቁ በሆነችው ካታር ሊጀመር በእጅጉ ተቃርቧል። በነዳጅ ሃብት የፈረጠመችው ሃገር እስከዛሬ ታይቶ…